የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
📢
አሰሪና ሰራተኛ: የሙከራ ጊዜ (Probation Period) ዋና ዋና የሰበር ችሎት ውሳኔዎች !
አሠሪዎችና ሠራተኞች ትኩረት! በኢትዮጵያ የሠራተኛ ሕግ የሙከራ ጊዜን በተመለከተ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችሎት የተሰጡ ቁልፍ የሕግ ትርጓሜዎችን ለሁሉም በሚያቀል መልኩ አቅርበናል። መብቶቻችሁንና ግዴታዎቻችሁን እወቁ!
1. የሙከራ ጊዜ ቆይታ እና ስንብት የሚፈቀድበት ጊዜ
•
⏱️
ከፍተኛው የጊዜ ገደብ:
o በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት 45 ተከታታይ ቀናት።
o በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት 60 ተከታታይ ቀናት መብለጥ የለበትም። (የሰበር መ/ቁ. 212420, 125899, 230567)
•
🗓
የጊዜ አቆጣጠር: የሙከራ ጊዜው ሲጠናቀቅ በቀጣዩ ቀን የስንብት ደብዳቤ መጻፍ የሕጉን መንፈስ አይቃረንም። (የሰበር መ/ቁ. 101890)
•
🤝
በውል የተስማሙበት ጊዜ: ግራ ቀኙ ለምሳሌ ለ"ሁለት ወር" ከተስማሙ፣ ፍርድ ቤት "የሥራ ቀናት" ብቻ ናቸው ብሎ አይተረጉምም፤ ከተጀመረበት ቀን አንስቶ ሁለት ወር ሲያልቅ፣ የሙከራ ጊዜውም ያበቃል። (የሰበር መ/ቁ. 250942)
• ቀጣይነት: የሙከራ ጊዜው አልቆ ሰራተኛው ስራውን ከቀጠለ፣ ውሉ ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ እንደሆነ ይቆጠራል። (የሰበር መ/ቁ. 174501)
2. የሙከራ ጊዜ መስፈርቶች
•
📝
የጽሑፍ ውል አስፈላጊነት: የሙከራ ጊዜ ውል ተደርጓል ለማለት በጽሑፍ የተደረገ ውል መቅረብ ግድ ነው። (የሰበር መ/ቁ. 215599, 225852, 238244)
•
✅
የስምምነት ማረጋገጫ: ሰራተኛው የሙከራ ጊዜን የሚያመለክት ደብዳቤ መፈረሙ ብቻ በውሉ ላይ ግልጽ ስምምነት ማግኘቱን አያረጋግጥም። አሠሪው በግልጽ አውቆና ተገንዝቦ በፅሑፍ ያሰፈሩት ስምምነት መኖሩን ማረጋገጥ አለበት። (የሰበር መ/ቁ. 140781, 98052)
•
⚖️
የማስረዳት ሸክም: ሰራተኛውን በሙከራ ጊዜ እንደቀጠረ የሚያቀርበው አሠሪው የማስረዳት ግዴታ አለበት። (የሰበር መ/ቁ. 194058)
3. በሙከራ ጊዜ የሥራ ውል ስለማቋረጥ
•
🧐
የመገምገም ግዴታ: አሠሪው ሰራተኛውን ማሰናበት የሚችለው የሥራ አፈጻጸሙን ገምግሞ ለሥራው ተስማሚ አለመሆኑን ሲያረጋግጥ ብቻ ነው። (የሰበር መ/ቁ. 212420, 247252)
•
🚫
ሕገወጥ ስንብት (ያለ ምዘና): ሰራተኛው ገና ስራውን ሳይጀምር ወይም ሳይሰራ/ሳይገመገም በዘፈቀደ ማሰናበት ሕገ-ወጥ ነው። (የሰበር መ/ቁ. 212420, 247252)
•
🔀
"ተስማሚ አለመሆን": "ለሥራው ተስማሚ አለመሆን" የሚለው ሐረግ የሥራ አፈጻጸምን ብቻ ሳይሆን በሥነ ምግባር ረገድ ለሥራ ተስማሚ መሆን አለመሆኑን ጭምር ይመለከታል። (የሰበር መ/ቁ. 170126)
•
💰
ያለመክፈል መብት: ሰራተኛው ብቁ አለመሆኑ ሲረጋገጥ፣ አሠሪው ያለማስጠንቀቂያ፣ የስራ ስንብት ክፍያና ካሳ ሳይከፍል ውሉን ሊያቋርጥ ይችላል። (የሰበር መ/ቁ. 125899)
4. በሕገ ወጥ መንገድ ለተሰናበተ የሙከራ ጊዜ ሠራተኛ የሚሰጥ ካሣ
•
💸
የካሳ መጠን: በሕገ-ወጥ መንገድ ለተሰናበተ የሙከራ ጊዜ ሠራተኛ የሚከፈለው ካሳ ከፍተኛው የሙከራ ጊዜ ጣሪያ (60 ቀን) ድረስ ቢሰራ ኖሮ ሊያገኝ ይችል የነበረውን የ2 ወር ደመወዝ (ወይም የቀሩት የሙከራ ጊዜ ደመወዝ) ብቻ ይሆናል። (የሰበር መ/ቁ. 212420, 247252)
•
❌
እገዳ: የሙከራ ጊዜ ሰራተኛ የአገልግሎት ዘመንን ታሳቢ ተደርጎ የሚሰላ የስንብትና የማስጠንቀቂያ ክፍያዎች አይከፈለውም። (የሰበር መ/ቁ. 247252)
5. የሙከራ ጊዜ መጠናቀቅ ህጋዊ ውጤት
• የቋሚነት ጥያቄ: የሙከራ ጊዜያቸውን የጨረሱ ሰራተኞች "ቋሚ ሰራተኛ እንሁን" የሚለው ጥያቄ የክስ ምክንያት የሌለው (የሕግ መሰረት የሌለው) ነው። (የሰበር መ/ቁ. 236244)
•
🔄
ተደጋሚ ቅጥር: ሰራተኛን ቀድሞ ይሰሩበት ለነበረው ስራ ለሙከራ መቀጠር በሕጉ ያልተፈቀደ ነው። (የሰበር መ/ቁ. 164135)
1 comment
Melk
Jan 13
አንድ ሰራተኛ በኮንትራት ከተቀጠረ ደሞዝ ተቀንሶ እንደ አዲስ ኮንትራት ማስፈረም ይቻላል እንዴ