👉ማስታወቂያ ለማህበር ቤት ተጠባባቂ ምዝገባ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በ2005 ዓ.ም የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝግበው በመቆጠብ ላይ ካሉ ቤት ፈላጊዎች ውስጥ በማህበር ተደራጅቶ በጋራ ቤት ለመስራት አቅም እና ፍላጎት ያላቸውን ተመዝጋቢዎች በማህበርአደራጅቶ መሬት በማስረከብ በተለያዩ ሳይቶች ግንባታ እንዲጅምሩ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ከማህበሩ ውስጥ አባላት በተለያዩ ምክንያት ሲጓደሉ ቢሮው ተጠባባቂዎችን መዝግቦ በማዘጋጀት በሚጓደሉ አባላት ተተኪ አባላት ይመድባል፡፡

በመሆኑም በተጠባባቂነት በመመዝገብ በማህበር ተደራጅቶ ቤት ለመገንባት አቅም እና ፍላጎት ያላችሁ የ2005 ዓ.ም የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ብቻ በተዘጋጀው ሲስተም ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ማስታወቂያው ከወጣበት 07/01/2019 ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡


ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

1. የ2005 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢ የሆኑ እና እየቆጠቡ የሚገኙ፡፡

2. ለቤት ግንባታ የሚውለውን 70 በመቶ ገንዘብ ማህበራቱ እያስገነቡ በሚገኝበት ዋጋ መሰረት ማዋጣት የሚችል እና ቀሪውን 30 በመቶ ቢሮው ባመቻቸው መሰረት ከባንክ ለመበደር ፍቃደኛ የሆኑ፡፡

▶️ማሳሳቢያ:- ምዝገባው የሚደረገው ኦንላይን ብቻ በመሆኑ ቢሮ መምጣት አያስፈልግም (የሞባይል ስልክዎን ተጠቅሞ መመዝገብ ይችላሉ)

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

የመመዝገቢያ ሊንክ፡- https://forms.gle/3y6E2EmAZSbboRg8A

@etconp

Comments

Be the first to add a comment