👉ስኬታማ የኮንስትራክሽን መሪ ለመሆን

🌟በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ውጤታማ መሪ መሆን ማለት ፕሮጀክቱን ከማከናወን ባለፈ ሰዎችን ማስተባበር፣ ደህንነትን ማረጋገጥና ጥራትን በወቅቱ ማስረከብ ማለት ነው። ለዚህ አዲስ ሳምንት ሥራዎ ስኬታማ እንዲሆን እነዚህን 8 ነጥቦች ልብ ይበሉ፦

ለደህንነት ቅድሚያ (Safety First)

ደህንነት አማራጭ ሳይሆን የሥራችን መሠረት ነው። እያንዳንዱ ሠራተኛ በሰላም መጥቶ በሰላም ወደ ቤቱ የሚመለስበትን የሥራ ባህል ይገንቡ።

ግልጽ ግንኙነት
(Clear Communication)

የፕሮጀክቱ ግቦችና የሚጠበቁ ውጤቶች ለቢሮም ሆነ ለሜዳ (Field) ሰራተኞች ያለ ብዥታ መድረሳቸውን ያረጋግጡ። ግልጽነት ስህተትን ይቀንሳል።

ቆራጥነትና ስጋትን መቀነስ (Decisiveness & Risk Mitigation)

እንደ የአየር ሁኔታ ወይም የግብዓት መዘግየት ያሉ ተግዳሮቶች ሲመጡ በፍጥነት በመወሰንና አማራጭ መፍትሄዎችን በማዘጋጀት ፕሮጀክቱን ከቀውስ ይታደጉ።

መተማመንን መገንባት
(Relationship Building)

የቡድን አባላትን በአክብሮት ይያዙ፤ በመካከላችሁ መተማመን ካለ ስራው በቅንጅት ይከናወናል።

ኃላፊነትን ማጋራት
(Delegation & Accountability)

ሁሉንም ስራ ብቻዬን ልስራ ሳይሉ ተግባራትን ለባለሙያዎች ያከፋፍሉ፤ ውጤቱንም በኃላፊነት ስሜት ይከታተሉ።

በአርአያነት መምራት
(Lead by Example)

ሰራተኛው እንዲያከብረው የሚፈልጉትን ስነስርዓት፣ ታማኝነትና የስራ ትጋት እርስዎ አስቀድመው በተግባር ያሳዩ፤

ቴክኒካዊ እውቀት
(Technical Knowledge)

የመሪነት ክህሎትዎን ከዘመናዊ የኮንስትራክሽን ስነ-ዘዴዎችና ቴክኖሎጂዎች ጋር በማጣመር ሁሌም የተሻለ መፍትሄ አቅራቢ ይሁኑ።

ቀጣይነት ያለው ትምህርት
(Continuous Learning)

ዓለማችን በየቀኑ እየተለወጠች ነው። አዳዲስ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን ለመቀበል ሁሌም ዝግጁ ይሁኑ።

ያስታውሱ፦ ጠንካራ መሪ ችግር ከመጣ በኋላ ምላሽ የሚሰጥ ሳይሆን፣ ችግሮች እንዳይከሰቱ አስቀድሞ የሚከላከልና ቡድኑን ለስኬት የሚያዘጋጅ ነው።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment