🏗️ በኮለን ላይ ይህን ችግር ምን ያመጣዋል? እንዴትስ እንከላከል?
🤔🚥በኮንክሪት ኮለን (Column) ላይ እንደሚታየው ይህ የማር ወለላ መሰል ቀዳዳና የኮንክሪት መበታተን Honeycombing ይባላል።
🔆ይህ የኮንክሪት ጥራት ችግር ብቻ ሳይሆን፣ የመዋቅሩን ጥንካሬና ዘላቂነት ሊጎዳ ይችላል።
🔍 Honeycombing ለምን ይፈጠራል?
🔸 ኮንክሪትን በትክክል አለማንቀጥቀጥ (Poor vibration)
🔸 ኮንክሪት በጣም ደረቅ መሆን (Low workability)
🔸 በብረት መካከል ኮንክሪት በትክክል አለመግባት
🔸 የፎርም ስራ ክፍተት መኖርና ኮንክሪት ማፍሰስ ጊዜ መፍሰስ
🔸 ኮንክሪትን በአንድ ጊዜ ብዙ ከፍታ ላይ ማፍሰስ
✅ እንዴት እንከላከል?
✔️ በቂ የኮንክሪት ውህደት (Proper vibration) ማድረግ
✔️ ትክክለኛ የኮንክሪት ውህደትና Workability ማረጋገጥ
✔️ ብረቶቹ መካከል ኮንክሪት በቀላሉ የሚያልፍ ቦታ ማረጋገጥ
✔️ ፎርምወርክ ጥብቅና የተዘጋ መሆኑን ማረጋገጥ
✔️ ኮንክሪትን በተገቢ የንብርብር ሁኔታ ማፍሰስና በትክክል ማንቀጥቀጥ
⚠️ አስታውስ! የHoneycombing ችግር በላይ በሚታየው መጠን ብቻ አይወሰንም። በኮለን ላይ ከተከሰተ በተለይ የጥንካሬና የዘላቂነት ጉዳይ ስለሆነ በኢንጂነር ተመርምሮ ተገቢው የጥገና ዘዴ መወሰን አለበት።
👷♂️ በግንባታ ላይ የኮንክሪት ጥራት ማለት የህንፃው ደህንነት ማለት ነው!
@etconp