ጤና ይስጥልኝ!
በቅርቡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት ሲያቀርቡ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት በአባልነት ለመመልመል ተፈልጎ ከተጠበቀው በታች መሆኑንና ይህም ደግሞ እንደ’ርሳቸው አባባል ለወደፊቱም ጥሩ አለመሆኑና ሊታሰብበት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩትን በመያዝ፣የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ስለተቋሙ(ስለ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር መ/ቤት በቂ ግንዛቤ ስላልሰረጸ ሊሆን ይችላል ከሚል ግምት መጠነኛ ማስገንዘቢያ ለመፍጠር ይረዳ ዘንድ ስለዚሁ ከወጣው ‘’የመከላከያ ሠራዊት አዋጅ ቁጥር 1100/2011’’ ድንጋጌ ይህ ጽሑፍ ቀርቧል።
መልካም ንባብ!
ተቋሙን በበላይነት የሚመራው የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስቴር ሲሆን ሚኒስቴሩ የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ሚዛናዊ ተዋፅዖን የሚያካትት ሆኖ ለወታደርነት ብቁና ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን ለመመልመል የሚያስችል መመዘኛን በየጊዜው የሚያወጣና በዚሁ መሠረት የተመለመለ ማንኛውም ሰው የውትድርና አገልግሎት ከመጀመሩ በፊት መሠረታዊ ስልጠና የሚሰጠው ሲሆን በአገልግሎት ላይ ያለ የሠራዊት አባልም እንደየግዳጁ አስፈላጊነት፣ዝንባሌውና ችሎታው እየተመዘነ በልዩ ልዩ የሙያ መስክ እንዲሰለጥን ወይም እንዲማር የሚደረግ ሲሆን እንደዚሁም የሠራዊቱ አባል የሚወጣውን መመዘኛ የሚያሟላ ከሆነ በመኪንንነት(ሚኒስቴሩ ከሲቭል ዜጋም በዕጩ መኮንንነት ከሕብረተሰቡ በቀጥታ የሚመለመልበት ሁኔታም እንዳለ ሆኖ) እንዲያገለግል በዕጩ መኮንንነት መልምሎና ስልጠናውን በስኬት ካጠናቀቀ የምክትል መቶ አለቃ ማዕረግን የሚያገኝ ሲሆን መኮንን ማለትም ከምክትል መቶ አለቃ እሰከ ጀነራል ማዕረግ ያለውን የሚያጠቃልል መሆኑን ስንገልጽ ለወደፊቱ በምድር ኃይል እና በአየር ኃይል ያለውን የማዕረግ ደረጃዎችን እና ለመከላከያ ሠራዊት አባላት ስለሚሰጡ ሽልማቶች ከአዋጁ ላይ በመነሳት የምንገልጽ ሲሆን ለዚህ ጹሑፍ መቋጫ ግን ከዚህ የሚከተለውን እናስቀምጥ፦
በሠራዊቱ ውስጥ በውትድርና አገልግሎት ላይ የሚገኝ ማንኛውም የሠራዊቱ አባል ቀለብ፣የመኖሪያ ቤት፣የመጓጓዣና የሕክምና...አገልግሎቶችን በነጻ የሚያገኝ ሲሆን እንደዚሁም አባሉ ወይም የቤተሰቡ አባላት በሚኖሩበት አከባቢ በሚገኙ የመንግስት የሕክምና ተቋማት በነጻ የመታከም መብት ያላቸውና ለማበረታቻነት እንደ-የአገልግሎት ዓመቱ ጊዜና ማዕረግ መኪና ከቀረጥ ነጻ የመግዛትንም ሆነ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንዲያገኝ በመንግሥት ደጋፍ እንደሚደረግ የተደነገገ መሆኑና ለመግለጽ እንወዳለን።
ደረጀ ማርቆስ
ጥር 2013 ዓ.ም

Comments

Be the first to add a comment