ለኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች‼️

በተለያዩ ሚዲያዎች active አስደርጉ በሚል እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ሀሰት ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ለ2ዐ/8ዐ እና ለ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎችን በተመለከተ ሰሞኑን በተለያዩ ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ቀነ ገደብ በማስቀመጥ የምዝገባ ቋት ውስጥ መኖራችሁን አረጋግጡ እንዲሁም ምዝገባችሁን ንቁ (active) አድርጉ በማለት እየተናፈሰ የሚገኘውን ሀሰተኛ ወሬ ተከትሎ ተመዝጋቢዎች በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተደደር ቢሮ በመገኘት ለአላስፈላጊ ምልልስ እየተዳረጉ ይገኛሉ፡፡

ይሁንና ተመዝጋቢዎች ያለምንም ቀነ ገደብ በተቋሙ ዌብሳይት መረጃውን ማግኘት ስለሚችሉ በአካል መምጣት ሳያስፈልግ ማንኛውም ተመዝጋቢ የምዝገባ ሂሳብ ቁጥሩን በማስገባት ንቁ (active) መሆኑን ማረጋገጥ የሚችልና አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

የትም መሄድ ሳይጠበቅባችሁ የቁጠባ ገንዘብ ስትከፍሉ በራሱ active ይሆናል።

ስማችሁ ከሌለ ብቻ ነው ወደ ቢሮ መሄድና ማናገር የሚጠበቅባችሁ የሚል መረጃ ደርሶናል።
ከሀሰተኛ መረጃ እራስዎን ይጠብቁ።
ሼር ይደረግ።

👉ለማረጋገጥ ትክክለኛ ዌብሳይት👇👇👇

http://aahdab.et/saving?fbclid=IwY2xjawPWf8tleHRuA2FlbQIxMQBzcnRjBmFwcF9pZA80MDk5NjI2MjMwODU2MDkAAR4F8YnupudfwCHjfxzy1lS_b2S48eWB7B7FH2rQ9O-fKqyrhYQAMvPeBknBzQ_aem_5vXamwn4SHNHQKQsSVT2sg

@etconp

Comments

Be the first to add a comment