👉በሊዝ የተያዘ መሬት ላይ ግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ

✂️ሀ) ግንባታ ማስጀመሪያ

አንድ ግለሰብ/ድርጅጥ በከተማ ቦታ ላይ በሊዝ የተረከበው ቦታ ላይ የሊዝ ውል ከፈረመበት ቀን ጀምሮ ለቦታው በተቀመጠው ደረጃ መረሰት ግንባታ እንዳለበት የሚደነግግ የጊዜ ጣሪያ ተቀምጧል።

በሊዝ ቦታ ላይ የግንባታ መጀመሪያ የጊዜ ጣሪያ፦ ለአንሰተኛ ደረጃ ግንባታዎች = 6 ወር፣ ለመካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች = 9 ወር፣ እና ለከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች = 18 ወር ነው።

ሆኖም ግን እስንደአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ ወይም በተለያዩ ምክንያቶች በተጠቀሱት የጊዜ ገደቦች ግንባታ ሳይጀመር ቢቀር ለአንድ ዙር ብቻ የሚፈቀድ ለአንሰተኛ ደረጃ ግንባታዎች  6 ወር፣ ለመካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች 9 ወር፣ ለከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች አንድ ዓመት ተጨማሪ የግንባታ ማስጀመሪያ ጊዜ በግንባታ ፍቃድ ሰጪው አካል ከማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ጋር ሊሰጣቸው ይችላል።

✂️ለ) ግንባታ ማጠናቀቂያ

በሊዝ ቦታ ላይ ግንባታ የማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ፦ ለአንሰተኛ ደረጃ ግንባታዎች 24 ወራት፣ ለመካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች 36 ወራት፣ እና ለከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች  48 ወራት ነው።

ነገር ግን የአካባቢው የግንባታ ፍቃድ ሰጪ አካል ካመነበት የግንባታውን ውስብስብነት እያየ ሊያራዝምለት ይችላል።

ሆኖም ግን ለግንባታ ማጠናቀቂያ የሚሰጠው ጊዜ በማንኛውም ምክንያት (ሁኔታ) ቢሆን ለአንሰተኛ ደረጃ ግንባታዎች  2 ዓመት 6 ወር፣ ለመካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች 4 ዓምት፣ እና ለከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች ከአምስት ዓመት መብለጥ የለበትም።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment