በጠበቆች ወይም የጥብቅና ድርጅት የሚፈጸሙ ቀላል የዲስፕሊን ጥፋቶች እና የሚያስከትሏቸዉ ተጠያቂነቶች
1. የጥብቅና ፈቃድን ለደንበኛ፤ ለፍርድ ቤት ወይም ለሚመለከተዉ አካል እንዲያሳይ በተጠየቀ ጊዜ ለማሳየት ፈቃደኛ ያለመሆን
2. ጉዳዩ ያለበትን ሁኔታና የደረሰበትን ደረጃ በደንበናዉ ሲጠየቅ በአግባቡ ያለማሳወቅ ደንበኛን ማመናጨቅ ወይም ክብሩን መንካት
3. ያለበቂና አሳማኝ ምክንያት በቀጠሮ ቀን መዘግየት እና ፍርድ ቤት ያለመገኘት
4. ለጠበቆች ማኅበር መክፈል የሚጠበቅበትን ክፍያ ወይም መዋጮ በተደጋጋሚ እና በወቅቱ ያለመክፈል
5. የጥብቅና ፍቃድን በወቅቱ አለማሳደስ
6. ባልታደሰ የጥብቅና ፍቃድ የጥብቅና አገልግሎት መስጠት
7. የጥብቅና ፍቃዱን ለጥብቅና ፍቃድ ሰጪው ተቋም ሳይመልስ በሌላ ቋሚ ሥራ ተሰማርቶ መገኘት
በተራ ቁጥር 1 እና 2 ከተደነገጉት ጥፋቶች አንዱን የፈጸመ ጠበቃ ዌም የጥብቅና ድርጅት የቃል ማስጠንቀቂያ በዲስፕሊን በዲስፕሊን ጉባዔው ይሰጠዋል፤ ለሁለት ጊዜ የቃል ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት ለሶስተኛ ጊዜ ተመሳሳይ ጥፋት ከፈጸመ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል
በተራ ቁጥር 3 እና 4 የተደነጉትን ጥፋቶች የፈጸመ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፡፡
በተራ ቁጥር 5--7 የተደነገጉትን ጥፋቶች የፈጸመ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት እንደነገሩ ሁኔታ ከብር አምስት ሺህ እስከ ብር ሰባት ሺህ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡
1249/2013 አን 83 እና 84
ህድአት ጌታቸዉ ታህሳስ/2014 ዓ.ም

Comments

Be the first to add a comment