የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
የቀጠለ
መመሪያ ማውጣትን በተመለከተ ማንኛውም የአስተዳደር ተቋም በሕግ በተሰጠው የውክልና ሥልጣን መሠረት መመሪያ ማውጣት እንደሚችል የተደነገገ ሲሆን ማንኛውም ሰዉ መብቱን ወይም ጥቅሙን በሚመለከት የአስተዳደር ተቋም መመሪያ ያላወጣ ቢሆንም የአስተዳደር ውሳኔ እንዲሰጠው የመጠየቅ መብት አለው፡፡ይህም ማለት ማንኛዉም የአስተዳደር ተቋም ሊያወጣ የሚገባውን መመሪያ አለማውጣቱ በሕግ በተሰጠው ኃላፊነት ሊሰጥ የሚገባዉን አገልግሎት ወይም አስተዳደራዊ ዉሳኔ ላለመስጠት ምክንያት ሊሆነው አይችልም፡፡
ይህ እንዳለ ሆኖ ማንኛውም ሰው አንድ የአስተዳደር ተቋም ሊያወጣው የሚገባዉን መመሪያ በተገቢው ጊዜ ሳያወጣ ቢቀር መመሪያውን እንዲያወጣ በጽሁፍ ሊጠይቀው ይችላል፤ጥያቄው የቀረበለት የአስተዳደር ተቋምም በሠላሳ የሥራ ቀናት ውስጥ መመሪያውን የማውጣት ሂደት መጀመር ወይም ምክንያቱን በመግለጽ ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ መመሪያ በሚያወጣበት ጊዜ የሚከተሉትን የያዘ መዝገብ ማደራጀት አለበት፦
ሀ) በተቋሙ በመታየት ላይ ያለ ረቂቅ መመሪያ ርዕሰ ጉዳይ እና የመመሪያውን አወጣጥ መርሃ ግብር፤
ለ) የረቂቅ መመሪያው ዝግጅት በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የሚያመለክት መረጃ፤
ሐ) ረቂቅ መመሪያውን በተመለከተ የታተሙ ማስታወቂያዎች፤
መ) በረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያየት ስለሚቀርብበት ጊዜ፤
ሠ) ረቂቅ መመሪያውን በተመለከተ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 8 እና 9 መሠረት የተሰበሰቡ አስተያየቶችንና በአስተዳደር ተቋሙ በአስተያየቶቹ ላይ የተወሰዱ አቋሞችን፡፡
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 8 እና 9 የሰፈሩት ነጥቦች ማስታወቂያ ስለማዉጣት እና ረቂቅ መመሪያን ለአስተያየት ስለመላክ ሲሆን እነዚህን ነጥቦች ጠቅለል ባለ መልኩ ስናሰፍር የአስተዳደር ተቋም መመሪያ ከማውጣቱ በፊት ስለሚያወጣው ረቂቅ መመሪያ ሰፊ ስርጭት ባለው ጋዜጣ እና የተቋሙን ድረ ገጽ ጨምሮ በሌሎች የመገናኛ ብዙሃን የመመሪያውን ረቂቅ ለማዘጋጀት መሰረት የሆነውን ሕጋዊ ሥልጣን እና በመመሪያው ስለሚካተቱት ርዕሰ ጉዳዮች መረጃዎች የያዘ ማስታወቂያ፣የረቂቅ መመሪያውን ቅጂ ማግኘት የሚቻል ስለመሆኑና የሚገኝበትን ሁኔታ፤በረቂቅ መመሪያው ላይ ሰዎች አስተያየታቸውን መቼ እና እንዴት ሊያቀርቡ እንደሚችሉ፤ማካተት ያለበት ሲሆን ለሕዝብ ያሳወቀውን ረቂቅ መመሪያ ለሚመለከታቸው የአስተዳደር ተቋማትና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ለአስተያየት መላክ አለበት፡፡የሚመለከታቸው የአስተዳደር ተቋማትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ደግሞ በረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያየት ካላቸው አስተያየታቸውን ተቋሙ በሚወስነው የጊዜ ገደብ ውስጥ በጽሁፍ መላክ ያለባቸው ሲሆን ተቋሙ የሚወስነው የጊዜ ገደብ በማናቸውም ሁኔታ ከ15 የሥራ ቀናት ማነስ የለበትም።
ሰናይ ዕለተ አርብ! (7/5/2013 ዓ.ም) (ኦምኒኤል)
ይቀጥላል
Comments
Be the first to add a comment