የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ሰላም ከርሰዎ ጋር ትሁን!!!
በመመሪያ 17/2006 ስለሰነድ አልባ መስተንግዶ ከተዘረዘሩት ዋናዋና ነጥቦች ስለአፈር ኪራይ ስለተደነገገው እነሆ ያንብቡልኝ!!
የመሬት ኪራይና የቤት ግብር ገብረው የማያውቁ ወይም በስማቸው የመሬት ኪራይና የቤት ግብር ማስታወቂያ ቢል ያልተሰጣቸው ወይም ሲገብሩ ቆይተው በማቋረጣቸው ከወረዳው ገቢዎች ማህደራቸው ባለመገኘቱ መስተናገድ ያልቻሉት ይዞታዎች መስተንግዶ አሰጣጥን በሚመለከት፣
ይዞታው ከግንቦት 1988 ዓ.ም በፊት የተያዘ መሆኑ ከሶፍራቶፕ ወይም ከኖርቴክ ወይም ከጂአይኤስ መረጃዎች በክ/ከተማው ሰነድ አልባ መስተንግዶ ፕሮጀክት ዴስክ ተጣርቶ ሲረጋገጥ፣
የወረዳው አስተዳደር መስተንግዶ ጠያቂው የይዞታው ባለመብት መሆኑን በደብዳቤ ሲያረጋግጥ፣
በክ/ከተማው የፕሮጀክት ጽ/ቤት ከሚገኘው የሲአይኤስ መረጃ ቢሉ ታትሞ በጽ/ቤቱ ቢል አታሚ፣ በይዞታ አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ እና በጽ/ቤቱ ኃላፊ ተፈርሞ ለወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት በደብዳቤ በመላክ የመሬት ኪራዩንና የቤት ግብሩን መክፈል እንዲጀምሩ በማድረግ መስተንግዶ ይሰጣቸዋል፡፡
መጋቢት 9/2014 ዓ.ም(ሲሳይ ሰማኝ)
Comments
Be the first to add a comment