ከሀምሌ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በግል አቤቱታ አቅራቢነት ክስ የሚመሠረትባቸው የወንጀል ጉዳዮች እና በግለሰቦች መካከል የሚደረጉ እስከ ብር 500,000 የገንዘብ፣ ውልና ብድር የፍትሐ ብሄር ጉዳዮች በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና በፌዴራል ፍርድ ቤት መታየታቸው ቀርቶ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ ቢሮ እና በአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች መታየት ይጀምራሉ፡፡

በዚህም ምክንያት ከተጠቀሰው እለት አንስቶ ቦሌ ክፍለ ከተማ ዐቃቤ ህግ ጽ/ቤት እነኚህን ጉዳዮች ተቀብሎ የሚያስተናግድ በመሆኑ በተበዳዩ አቤቱታ መሰረት ክስ የሚያስመሰርቱ ጉዳዮች እንዲመረመሩለት የሚፈልግ ወይም የዋጋ ግምቱ ከ500,000 ብር በታች የሆነ የፍትሀብሄር ክስ ማቅረብ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው አቤቱታውን ወንጀሉ የተፈጸመበት ቦታ ለሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ወይም ለክ/ከተማ ዐቃቤ ሕግ ፅ/ቤት በመቅረብ መስተናገድ የምትችሉ ሲሆን ክሱ የሚታየውም (የዳኝነት ስልጣን) በአዲስ አበባ ፍ/ቤቶች መሆኑን ጨምረን እንገልጻለን ።

Comments

Be the first to add a comment