ኢትዮ ቴሌኮም ከወረቀት ወደ ኤሌክትሮኒክ የሞባይል ካርድ ሽያጭ በሚያደርገው ሽግግር ቀላልና የተቀላጠፈ ለማድረግ የኤሌክትሮኒክ ቫውቸር ካርድ በቀላሉ በብዛት ለማዘዝና ለመሸጥ እንዲያስችል ተደርጎ የተሰራውን አፕ በመጫን የ10% ቅናሽ ተጠቃሚ ይሁኑ። በአፕሊኬሽኑ ለሚገዙ የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ደሞ የ5% የቦነስ ጭማሪ ይሰጣቸዋል። ለምሳሌ አንድ በሞባይል ችርቻሮ ለሚሰራ ሰው የ100 ብር ካርድ በ90 ብር ይገዛል ማለት ነው። ለገዢ በ100 ብር ሲሸጥ የገዛው ሰው 5 ብር ቦነስ ሲጨመርለት የ105 ብር ካርድ ይሆንለታል ማለት ነው። በዚህ አፕ ተጠቅሞ በችርቻሮ በመሸት የ10% ቅናሽ ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች

1. አፑን ከ ፕለይ ስቶር በማውረድ መጫን
2. ስምዎን ስልክ ቁጥሮንና ፒን ኮድ በማስገባት መመዝገብ
3. ከተዘረዘሩት ወኪል አከፋፋዮች በመምረጥ መመዝገብ ብቻ ነው

ለበለጠ መረጃ የመረጡትን ወኪል ጋር በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

የይሙሉ ዲለር አፕ አጠቃቀም
👉 https://youtu.be/9TXFU7oNw5E

1 comment

Tewodros Abreha
What about for the ios users(iphone)?