ጤና ይስጥልኝ
ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ሁኔታ በማየት ከዚህ የሚከተለውን ስለመከላከያ ሠራዊት ከወጣዉ አዋጅ ቁጥር 1100/2011 መሠረት የሚከተለውን እንበል፡፡
መልካም ምንባብ፡-
ኢትዮጵያ ለዘመናት ከውጭም ሆነ ከውስጥ የተነሱባትን ጠላት በማንበርከክ ነጻነቷን ጠብቃ ታፍራና ተከብራ የኖረችው እና ያለችው በውድ ልጆቿ ብርቱ ተጋድሎ መሆኑን ይልቁንም በፋሺስት ኢጣሊያ ተመጣጣኝ ያልሆነ የጦር መሣሪያ ኃይልን ተማምኖ የመጣውን መላው ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነው በመነሳት ድባቅ በመምታት ለጥቁር ሕዝብ ፋና ወጊ የሆኑበትን እንደዚሁም ኢትዮጵያ በውስጥ የመንግሥት ለውጥ ጊዜ በበርካታ ጉዳዮች ተወጥራ የነበረበትን ጊዜ በመጠቀም የሱማሌውን ተስፋፊ የዚያድበሬን ጦር አይቀጡ በመቅጣት አኩሪ ተግባራትን የፈጸሙ ልጆች እንዳሏት የቅርብ ጊዜ ተጋድሎን እያነሳን ከዚሁ ጋር ከዚህ በላይ በገለጽነው የመከላከያ ሠራዊት አዋጅ ቁጥር 1100/2011 የሠራዊቱ አባል ለሀገር ከሚያበረክተው ከማንም የላቀ አገልግሎት ባይመጣጠንም ለማበረታታት ያህል የቤት መኪና ከቀረጥ ነፃ የመግዛት እና በተወለደበት የክልል ከተማ የመኖሪያ ቤት መስሪያ እንዲያገኝ በመንግስት ድጋፍ የሚደረግ መሆኑን የተደነገገውን ግንዛቤ እንያዝ ፡፡
መልካም ቀን
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ !!
ሕዳር 15ቀን 2014ዓ.ም
ደረጀ ማርቆስ

Comments

Be the first to add a comment