👉እስከ 5.72 ቢሊዮን ዶላር የሚደርሰው አዲሱ የቢዝነስ ዘርፍ፦ «ማስ ቲምበር» የግንባታ ገበያን እንዴት እያወደሰው ይገኛል?
ለበርካታ አስርት ዓመታት የከተሞችን ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች በብቸኝነት ሲቆጣጠሩ የነበሩት ኮንክሪት እና ብረት፣ አሁን በዘመናዊ የተቀነባበሩ የእንጨት ውጤቶች (Mass Timber) እየተተኩ ይገኛሉ። በቅርቡ በሲድኒ አውስትራሊያ የተገነባው የ39 ፎቅ (180 ሜትር) «አትላሲያን ሴንትራል» ህንፃ እንደሚያሳየው፣ የተቀነባበረ እንጨት ከኮንክሪትና ብረት ጋር ተቀናጅቶ ረጅም ህንፃዎችን ለመገንባት የሚያስችል አዲስ የምህንድስና ምዕራፍ ከፍቷል።
ይህ ዘርፍ በአሁኑ ወቅት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበ ይገኛል።
የቅርብ ጊዜ የገበያ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በ2025 እ.ኤ.አ. 2.28 ቢሊዮን ዶላር የነበረው የዓለም አቀፍ የማስ ቲምበር ገበያ፣ በየዓመቱ የ13.9% እድገት በማሳየት በ2032 እ.ኤ.አ. 5.72 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
በተለይም በብዛት ጥቅም ላይ የሚውለው የCLT (Cross-Laminated Timber) ገበያ በ2030 እ.ኤ.አ. የ131% ያህል የሽያጭ ጭማሪ ያሳያል ተብሎ ተተንብዮአል።
በአህጉራት ደረጃ ሲታይ አውሮፓ የዚህን ገበያ 45.2% ($1.03 ቢሊዮን ዶላር) ድርሻ በመያዝ በግንባር ቀደምትነት እየመራች ይገኛል።
ሰሜን አሜሪካ በ33.5% ($765 ሚሊዮን ዶላር) ሁለተኛውን ደረጃ ስትይዝ፣ እስያ-ፓሲፊክ ደግሞ በ14.0% ድርሻ በፍጥነት በማደግ ላይ ያለ ገበያ ሆኗል። እንደ Stora Enso፣ Binderholz እና Mercer ያሉ ግዙፍ የኢንዱስትሪው አምራቾች የዘርፉን አቅርቦት በከፍተኛ ደረጃ እያሳደጉት ይገኛሉ።
የማስ ቲምበር ተወዳጅነት መጨመር ከቁሳቁሱ ባሻገር ከቴክኖሎጂ ውህደት ጋር የተያያዘ ነው። በአሁኑ ወቅት ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ለአንጨት ጥራት መለያ፣ ሮቦቲክስ ደግሞ ለትክክለኛ የእንጨት ቅርፅ መቁረጫነትና በቦታው ላይ ለመገጣጠም እየተጠቀሙባቸው ይገኛል።
በተጨማሪም በህንፃዎች ውስጥ የሚገጠሙ የ«ዲጂታል መንታ» (Digital Twins) ሴንሰሮች የእርጥበትና ንዝረት መጠንን በቅጽበት በመከታተል የህንፃዎችን ደህንነትና ዘላቂነት ያረጋግጣሉ።
በአጠቃላይ፣ ማስ ቲምበር የግንባታ ወጪንና ጊዜን ከመቀነሱም በላይ የካርቦን ልቀትን በመቀነስ ለአካባቢ ጥበቃ ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው። ምንም እንኳን የእሳት እና የእርጥበት መቋቋም ፈተናዎች ቢኖሩበትም፣ የቴክኖሎጂው ማደግ እና የቅይጥ (Hybrid) ግንባታዎች መስፋፋት የዓለም አቀፉን የግንባታ ዘርፍ ወደ አዲስ ዲጂታልና አውቶሜትድ ዘመን እያሸጋገረው ይገኛል።
@etconp