👉በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የ1.7 ቢሊዮን ዶላሩን የአዋሽ-ኮምቦልቻ-ሐራ ገበያ የባቡር መስመር ፕሮጀክት ግንባታን ተጀመረ።

የቀድሞው ተቋራጭ የቱርኩ 'ያፒ መርኬዚ' በጦርነቱ ለደረሰብኝ ጉዳት 1 ቢሊዮን ዶላር ካሳ ይከፈለኝ ብሎ በለንደን ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ፍርድ ቤት ከከፈተው የህግ ክርክር ጋር ጎን ለጎን ነው።

ኮርፖሬሽኑ እስካሁን ከተጠየቀው የካሳ ጥያቄ ውስጥ 70 በመቶውን በህግ መከላከል መቻሉን የገለጸ ሲሆን፣ የራሱን የሰው ኃይል እና ማሽነሪ በመጠቀምም 70 ኪሎ ሜትር የሚጠጋውን መስመር ጠግኖ ለሙከራ ዝግጁ አድርጓል፤ የመጀመሪያውን ምዕራፍም እስከ ኮምቦልቻ ድረስ በሁለት ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ አቅዷል።

ይህ እርምጃ በአንድ በኩል የአስገዳጅነት በሌላ በኩል ደግሞ የአቅም ማረጋገጫ ሙከራ ተደርጎ ይወሰዳል።

ኮርፖሬሽኑ ያቀረበው ጥናት እንደሚያሳየው፣ ከ68 በመቶ በላይ የሚሆነውን እንደ የመሬት ቁፋሮ እና የጣቢያ ግንባታ ያሉትን የፕሮጀክቱን ክፍሎች የሀገር ውስጥ ተቋራጮች በራሳቸው የመስራት አቅም አላቸው።

ሆኖም ግን ይህ ውሳኔ ሁለት ትላልቅ ማነቆዎችን አቅፏል ፥ በአንድ በኩል የለንደኑ የግልግል ዳኝነት ሂደት ገና ሙሉ በሙሉ ባለማለቁ እና ኮርፖሬሽኑም የቱርኩን ኩባንያ ማሽነሪዎች በስፍራው እየተጠቀመ በመሆኑ፣ ወደፊት ያልታሰበ የፋይናንስ እና የህግ ዕዳ ከመንግስት ትከሻ ላይ ላይወርድ ይችላል።

በሌላ በኩል ደግሞ፣ የሲቪል ስራውን የሀገር ውስጥ ባለሙያዎች ቢሰሩትም፣ የባቡር መስመሩን ስራ ለማስጀመር የግድ የውጭ ምንዛሬ እና የውጭ እውቀት የሚጠይቁትን የኤሌክትሪክ ዝርጋታ፣ የምልክትና መገናኛ ቴክኖሎጂዎችን አሁን ባለበት የፋይናንስ አቅም እንዴት ሊያሳካው ይችላል የሚለው ትልቁ የፕሮጀክቱ ፈተና ሆኖ ይቀጥላል።

Via ሪፖርተር ጋዜጣ

@etconp

1 comment

nurlign yimam
The work of the can