ጤና ይስጥልኝ

የሰው ልጅ በሕይወት ዘመኑ ከራሱም ሆነ ከሌላ በመጣ በጤናው ላይ እክል ሊያጋጥመው የሚችልና ለሕክምናው የሚያስፈልገውን ወጪ መንግሥት ለዜጎች የሕክምና አገልግሎት በእኩልነት እንዲያገኙ ለማስቻል ከሚመድበው በጀት ጋር የሚቀናጅና የእርስ በእርስ መደጋገፍን ለማጎልበት በሚያስችል ሁኔታ ከሕብረተ-ሰቡ በሚወጣ መዋጮ የጤና አገልግሎት ሽፋን እንዲገኝ የሚደረግበትን ሁኔታ የሚያመላክት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ‘’የማኀበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ደንብ ቁጥር 86/2009” ላይ ከሰፈረው መጠነኛ ጽሑፍ እናስፍር፡፡
መልካም ምንባብ፡-
ማንኛውም የማኀበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባል የመመዝገቢያ ክፍያና መደበኛ መዋጮ በወቅቱ መክፈሉ ከተረጋገጠ፤በልዩነት የጤና አገልግሎት የማይሰጥባቸው (ምሣሌ ሰው ሰራሽ የአካል ማስተካከል (ለውበት ሲባል)) መኖራቸው እንዳለ ሆኖ፤ የተመላላሽ፣ የተኝቶ፣ የቀዶ ጥገና (surgery)፣ በሕክምና ባለሙያዎች የታዘዙ የምርመራ አገልግሎቶችና በፅንሰ-ስም መድኃኒቶችን (Generic drugs) ከተቋሙ ጋር ዉል ከተፈራረሙ የጤና ተቋማት የማግኘት መብትን የሚያስገኝ መሆኑን ልብ ይሏል ፡፡
ፈጠሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ
ደረጀ ማርቆስ
የካቲት 2014 ዓ.ም

Comments

Be the first to add a comment