👉የምህንዲስና ግምት
/Engineering Estimation/

💫የምህንዲስና ግምት/Engineering Estimation/ የወቅቱ የገበያ ዋጋ ታሳቢ ያደረገ መሆን ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ ግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 70/2017 አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 7፣ 8 እና 9 መሰረት ከመጠን በላይ የተጋነነ የጨረታ ዋጋ(excessively high bid price)፣ የተሰበረ የጨረታ ዋጋ(unusually low bid price) እና እጅግ የተሰበረ የጨረታ ዋጋ(excessive low bid price) በትክክል መለየት አይቻልም።

⭐️የተሰበረ የጨረታ ዋጋ እና እጅግ የተሰበረ የጨረታ ዋጋ ለመለየት ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ለግንባታ ሥራው በጥናት የገመተው ጠቅላላ ዋጋ አገልግሎት ላይ እንደሚውል በግልጽ ተደንግጓል።

🚧በጥናት የተገመተ ዋጋ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ግልጽ ነው።

የምህንዲስና ግምቱ በጥናት የተገመተ ትክክለኛ ወቅታዊ የገበያ ዋጋ መሆን ይኖርበታል።

ነገር ግን አንዳንድ መ/ቤቶች ወቅታዊ ያልሆነ የምህንዲስና ግምት በመጠቀም ተጫራቾችን ከጨረታ ውጪ ለማድረግ ይሞክራሉ።

በተጫራቹ ዋጋ ላይ ፍረጃ ከመደረጉ በፊት ትክክለኛ ወቅታዊ የገበያ ዋጋ ጥናት እና ወቅታዊ የምህንዲስና ግምት መኖር አለበት።

የምህንዲስና ግምትን በተመለከተ ግዥ ፈፃሚ መ/ቤቶች ጥንቃቄ ቢያደርጉ መልካም ነው።

👉Please Subscribe Our Youtube Channel👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

@etconp

Comments

Be the first to add a comment