ስለየኢትዮጵያ የሕንፃ አዋጅ ቁጥር 1356/2017 ምን ያህል ያውቃሉ?
አዋጁ እጅግ ሰፊና ዝርዝር መረጃዎችን የያዘ ሲሆን፣ በተለይ በግንባታ ጥራት፣ በአካል ጉዳተኞች ተደራሽነት እና በባለሙያዎች ተጠያቂነት ላይ ትኩረት ያደርጋል።
አዋጁን በወፍ በረር ለመቃኘት እንዲመቸን፣ ዋና ዋና ነጥቦቹን በሚከተለው መልኩ ከፍለን አቅርበንላችኋል፡
1. የሕንፃዎች ምደባ (Building Categories)
አዋጁ ሕንፃዎችን በውስብስብነታቸውና በከፍታቸው በ4 ዋና ምድቦች ይከፍላቸዋል፦
• ምድብ 'ሀ'፦ ባለ አንድ ፎቅ የመኖሪያ ሕንፃዎች (ከ7 ሜትር ያልበለጠ ርቀት ያላቸው)።
• ምድብ 'ለ'፦ ከ2 እስከ 4 ፎቅ ያላቸው የግል ወይም የጋራ መኖሪያዎች።
• ምድብ 'ሐ'፦ ከ5 እስከ 12 ፎቅ ያላቸው ሕንፃዎች።
• ምድብ 'መ'፦ ከ12 ፎቅ በላይ የሆኑ፣ ማንኛውም የሕዝብ መገልገያ፣ ፋብሪካዎችና ኢንዱስትሪዎች።
2. የአካል ጉዳተኞች ተደራሽነት (Accessibility)
ይህ አዋጅ ለአካል ጉዳተኞች ልዩ ትኩረት ይሰጣል።
• ማንኛውም የሕዝብ መገልገያ ሕንፃ "ሁሉን አቀፍ ንድፍ" (Universal Design) መከተል አለበት።
• ነባር ሕንፃዎች እንኳ ሳይቀሩ ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እንዲሆኑ ማሻሻያ እንዲደረግባቸው ያስገድዳል።
3. የፈቃድና የቁጥጥር ሥርዓት
• የሕንፃ ሹም፦ ግንባታዎችን የሚቆጣጠርና ፈቃድ የሚሰጥ ባለሙያ መመደብን ይደነግጋል።
• የመጠቀሚያ ፈቃድ (Occupancy Permit)፦ በተለይ ለምድብ 'መ' ሕንፃዎች ግንባታው ሲጠናቀቅ ደህንነቱ ተረጋግጦ የመጠቀሚያ ፈቃድ ማግኘት ግዴታ ነው።
• የዲዛይን ዋስትና፦ ከፍተኛ የሕንፃ ዲዛይን ባለሙያዎችና ተቋራጮች ለሚሰሩት ሥራ የኢንሹራንስ ወይም የገንዘብ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶች
አዋጁ ጥብቅ የሆኑ ቅጣቶችን ያስቀምጣል፦
• ያለ ፈቃድ መገንባት ወይም ከዲዛይን ውጭ መሥራት ተጠያቂነትን ያስከትላል።
• ለባለሙያዎች፦ በቸልተኝነት ወይም ሆን ብሎ መረጃ በመደበቅ ጥፋት ለሚያጠፉ ባለሙያዎችና የሕንፃ ሹሞች እስከ 10 እና 25 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራትና ከፍተኛ የገንዘብ መቀጮ ተደንግጓል።
• ለአሰሪዎች፦ ደረጃውን ያልጠበቀ ቁሳቁስ መጠቀም ወይም ያለ መጠቀሚያ ፈቃድ ሕንፃውን አገልግሎት ላይ ማዋል ያስቀጣል።
በቀጣይ በአዋጁ ክፍሎች ላይ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ ይዘን እንመለሳለን!

Comments

Be the first to add a comment