የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ጤና ይስጥልኝ ፡-
በኢትዮጵያ የፍትሐብሔር ሕግ የሟች ዉርስ በኑዛዜ ወይም ያለኑዛዜ ሊተላለፍ እንደሚችል የተደነገገ ሲሆን ሟቹ ንብረቱን ለተወላጆቹ ወይም ተወላጆቹ ላልሆኑ ሰዎች በኑዛዜ ማስተላለፍ የሚችል ሲሆን ስለዚሁ የኑዛዜ አንዳንድ ሁኔታዎች የሚከተለዉን እንበል፤
መልካም ምንባብ፡-
በሕጋችን ሦስት ዐይነት የኑዛዜ ፎርሞች ያሉና ተናዛዡ አለኝ የሚለዉን ንብረት ከሦስቱ ፎርማቶች በአንዱ ለኑዛዜ ተጠቃሚዉ ማስተላለፍ የሚችል ሲሆን ተናዛዡ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ (ልጆች) የሆኑትን “በሕይወቴ ላይ ከፍተኛ ችግር ፈጥረዉብኛል “ በሚል በቂና ሕጋዊ ባልሆነ ምክንያት ወይም በዝምታ ከዉርሱ መንቀሉም ሆነ ሟቹ ካለዉ ሀብት ላይ እጅግ አነስተኛ የሆነ ንብረት ለተወላጁ በኑዛዜ የሰጠ እንደሆነ ተወላጁ ተነቅሏል ተብሎ ግንዛቤ ሲያዝበት የሚችል በመሆኑ ከዚህ በላይ የተገለጸዉ ከሆነ ተወላጁ ከሌሎች የጠቅላላ ኑዛዜ ተጠቃሚዎች ጋር እኩል መካፈል ያለበት መሆኑን ከፍ/ብ/ሕጉ ላይ ከተገለጹት ድንጋጌዎች በመነሳት በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ሰሚዉ ችሎት በሰ/መ/ቁ 58338 በሆነ የአስገዳጅነት ዉሣኔ ሰጥቶበታል ፡፡
ደረጀ ማርቆስ ነሐሴ 6/2013
Comments
Be the first to add a comment