የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ባለስልጣን አደረጃጀትና አሠራርን ለመወሰን የወጣ ደንብ ቁጥር 71/2008 መሰረት የትራንስፖርት ባለስልጣን የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት አሉት፡-
o በከተማው የብዙሀንና የጭነት ትራንስፖርትን በተመለከተ ተገቢውን መረጃ ማደራጀትና ማሰራጨት፤
o በከተማው የሚንቀሳቀሱ የብዙሃንና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አካላት አጠቃላይ የኦፕሬሽን ሥርዓታቸውን በበላይነት መቆጣጠር፣ ፈቃድ መስጠት እንዲሁም ማገድ፤
o የከተማውን የተማከለ የብዙሃን ትራንስፖርት ሥርዓት እንዲፈጠር ማድረግ፣ የስምሪት ድልድል ማዘጋጀት፣ ታሪፍ አጥንቶ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ፣ ሲጸድቅ ለተፈፃሚነቱም መስራት፣ ለአፈጻጸም የሚረዱ የቴክኖሎጂ አውታሮችንም መዘርጋት፤
o የከተማውን የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ማለትም ለሕዝብና ለጭነት ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውሉ መናኸሪያዎችን፣ ፌርማታዎችን፣ መጋዘኖችና ዴፖዎችን መገንባትና ማስተዳደር፤
o አጠቃላይ የከተማው የብዙሃንና የጭነት ትራንስፖርትን በተመለከተ መመሪያዎችን ማውጣት፣ ሲፈቀድለትም መተግበር፤
o የከተማውን የብዙሃንና የጭነት ትራንስፖርት አቅርቦትና ፍላጎት ማጥናት፣ አማራጭ መፍትሔዎችን በማቅረብ ለአቅርቦት መጣጣም ፕሮግራሞችን በመቅረፅ መስራት፤
o ለሕብረተሰቡ ተደራሽ የሆነ የትራንስፖርት መረጃ አገልግሎት ማደራጀት፣ ማሰራጨት፣ የከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት በቅንጅት እንዲሰሩ እቅድ ማውጣት፤
o የከተማውን የብዙሃንና የጭነት ትራንስፖርት መመዘኛ መስፈርቶች፣ ማኑዋሎች ደረጃዎች ማውጣትና ለተፈፃሚነቱ መስራት፤
o ለሚሰጠው አገልጎሎት ክፍያ መሰብሰብ፤
o ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በብዙሃንና በጭነት ትራንስፖርት ዘርፍ የሚሰሩ ኦፕሬተሮች፣ ማሕበራት፣ ድርጅቶችና ግለሰቦች እንዲደራጁና እንዲጠነክሩ ተገቢውን ድጋፍ መስጠት፣ ለከተማው ትራንስፖርት ቅልጥፍናና ደህንነት መስራታቸውን ማረጋገጥ፡፡ ናቸው
ፌናን ተጊበሉ
ታህሳስ 04/2014 ዓ.ም
Comments
Be the first to add a comment