👉በ6 ቢሊዮን ብር የተገነባው ዘመናዊ ሞል ተመረቀ

💫ባማኮን ሪል እስቴት በካዛንቺስ 2200 ካሬ ላይ ያረፈ ባለ 24 ወለል ጋላክሲ ፊኒሽንግ ሞል የመኖሪያ እና የንግድ አፓርትመንት በዛሬዉ እለት አስመርቆ ስራ አስጀምሯል።

🚧ይህ በከፍተኛ ጥራት እና በውብ ዲዛይን ተሠርቶ የተጠናቀቀው ጋላክሲ ፊኒሽንግ ሞል የኪነ ሕንጻ ባለሙዎችን፤ ሻጭ እና ገዥዎችን፤ አቅራቢዎችን፣ ዲዛይነሮችን እና ሌሎችንም በአንድ ጣሪያ በማሰባሰብ ወጪን የሚቆጥብ፣ ሕይወትን ቀላል እና ምቹ የሚያደርግ ድንቅ የመኖሪያ እና የንግድ አፓርትመንት መሆኑ ተነግሯል፡፡

ጋላክሲ ፊኒሺንግ ሞል የኤሌክትሪካል ሥራዎችን፤ የመታጠቢያ እና የንጽህና መጠበቂያ ክፍሎች መሥሪያ ቁሶችን፣ የወለል እና የግድግዳ ሥራዎች ማጠናቀቂያ ማቴሪያሎችን፣ እጅግ ዘመናዊ ውበትን የሚያላብሱ ልዩ ልዩ የፊኒሽንግ ማቴሪሎችን፤ በአጠቃላይ ሁሉንም የፊኒሽንግ ማቴሪያሎችን በአንድ ጣሪያ ስር አቀናጅቶ የያዘ ዘመናዊ ሞል መሆኑ ተነግሯል።

ጋላክሲ ፊኒሺንግ ሞል የግንባታ መሠረት ከማስቀመጥ እስከ ፊኒሺንግ ሥራ ድረስ በራሱ ድርጅቶች ሙሉ አቅም የተሠራ፤ በቂ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ያለው እንዲሁም በአከባቢው ላይ በከተማ አሥተዳደሩ እየተገነቡ ያሉ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያዎች እና የአደጋ ጊዜ የሚያስፈልጉ ቅድመ ጥንቃቄዎችን እና ሌሎችም አስፈላጊ መሰረቶች የተሟሉለት መሆኑን ተገልጿል።

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን ከፍተኛ የቤት ፍላጎት በማሻሻል ባማኮን ሪል እስቴት በመዲናዋ ዐይን የሚባሉ ቦታዎች ላይ ለኑሮ ምቹ የሆኑ የመኖሪያ እና የንግድ አፓርትመንቶችን በከፍተኛ ጥራት፣ ፍጥነት እና በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ፤ ለብዙዎች እፎይታ ማስገኘቱም ተገልጿል፡፡

ባማኮን ሪል እስቴት ከመሠረት እስከ ፊኒሽንግ በራሱ በባማኮን ግሩፕ እህት ኩባንያዎች ማለትም (ባማኮን ሪል እስቴት፣ አንከር ፋውንዴሽን ስፔሻሊስት፤ ባማኮን ኢንጅነሪንግ፣ አልፋ ፖስት ቴንሽኒንግ፣ ባማ ሚክስ ኮንክሪት፣ ታወር ኢንጅነሪንግ፣ አልትሜት ኬሚካልስ፣ ፊት አውት ኮንስትራክሽን) ግንባታዎችን እያከናወነ ይገኛል።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment