የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
#ለወራሽነት ብቁየሚያደርጉ_ነገሮች_ምንድን_ናቸዉ
ለወራሽነት ብቁ የሚያደርጉ በሕጉ የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎችን ሳያሟሉ ወራሽ መሆን አይቻልም፡፡ ይልቁንም አንድ ሰዉ ወራሽ ለመሆን በሕጉየተቀመጡትን ወራሽ ለመሆን መሟላት ያለባቸዉን ቅድመ ሁኔታዎች ሟሟላት አለበት፡፡ እነዚህን ሁኔታዎች ያላሟላ ወራሽ በኑዛዜ ስሙ ቢጠቀስም ወይም በሕግ ወራሽነቱ ቢገለፅም ከውርሱ ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም፡፡
ለወራሽ ብቁ ለመሆን የሚያስፈልጉት ቅድመ ሁኔታዎች፡-
(1) በሕይወት መኖር እና
(2)ለወራሽነት የማይገባ አለመሆን ናቸው፡፡
1) #በሕይወት_መኖር
✅
በፍ/ብ/ሕ/ቁ 830 ላይ እንደተገለፀው አንድ ሰው ወራሽ ለመሆን አውራሹ በሚሞትበት ወቅት በሕይወት ያለ መሆን አለበት፡፡
✅
በሌላ አገላለፅ ሟች ሲሞት ያልነበሩ ወይም ሟችን /አውራሽን / ቀድሞ የሞተ መውረስ አይችሉም፡፡ ነገር ግን በልዩ ሁኔታ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 834 ላይ እንደተገልፀው ሟች በሚሞትበት ወቅት በእናቱ ፅንስ ውስጥ ያለ ህፃን ተወልዶ 48 ሰዓት በሕይወት ከቆየ ውርስ ሲከፈት እንደነበረ ተቆጥሮ የመውረስ መብቱ ይጠበቅለታል፡፡
✅
እዚህ ነጥብ ላይ ሌላኛው አጨቃጫቂ ጉዳይ አብሮ በአንድ ጊዜ የሞቱ ሰዎች ጉዳይ ነው፡፡
አብሮ ሟቾቹ አንዱ አንዱን የሚወርስ ከሆነ የአንደኛው ውርስ ሲከፈት ሌላኛው በሕይወት መኖር አለት የሚለውን ቅድመ ሁኔታ ለማሟላት የትኛው ቅድሚያ እንደሞተ ማረጋገጥ አዳጋች የሚሆንበት ጊዜ ያጋጥማል፡፡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 832 ላይ ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ አስቀምጧል፡፡ ይህም ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች አብረው የሞቱ እንደሆነ እና የትኛው በኋላ የሞተው የሚለውን ማረጋገጥ ካልተቻለ ከአብሮ ሟቾቹ ሰዎች ኃብት ወራሽነት ምንም ሳያገኝ የነዚህ ሰዎች የያንዳንዳቸው ውርስ በመጨረሻ እንደ ሞተ ዓይነት ተቆጥር ይወሰናል፡፡
2) #ለወራሽነት_የማይገባ_አለመሆን
✅
ወራሽ ለመሆን ከሚያስፈልጉት ቅድመ ሁኔታዎች ሌላኛው ለወራሽነት የማይገባ አለመሆን ነው፡፡
✅
አንድ ወራሽ ለወራሽነት የማይገባ የሚሆነው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 838 ላይ እንደተጠቀሰው በአውራሹ ወይም ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጅ/ዎች/ ወይም ወደ ላይ የሚቀጠሩ ወላጆች ወይም ባል ወይም ሚስት አስቦ በመግደል የተፈረደበት ወይ ለመግደል ሙከራ የተቀጣ ወይም በሀሰት በመወንጀል ወይም
በመመስከር አንደኛውን የሞት ፍርድ ወይም ከአስር ዓመት በበለጠ የፅኑ እሥራት ቅጣትን ለማስከተል የሚያሰጋ ሆኖ የተቀጣ ከሆነ ነው፡፡ እነዚህን ከላይ
የተገለፁትን ድርጊቶች የፈፀመ እና የተቀጣ ሰው ወራሽ መሆን አይችሉም፡፡ ነገር ግን ወራሽ የሆነው ሰው በነዚህ በተጠቀሱ ሰዎች ላይ ወንጀሉን ወይም
የወንጀሉን ሙከራ ያደረገው አውራሹ ከሞተ በኃላ ከሆነ የወራሽነት መብቱን ማጣት አይፈፀምበትም፡፡
✅
ሌላው ለወራሽነት የማይገባ የሚያደርገው ምክንያት ሟች በነፃነት እንዳይናዘዝ ተጽእኖ ማሳደር ነው፡፡ ይህም አውራሽ ከመሞቱ በፊት ባሉት ሶስት ወር ውስጥ የአውራሽን ሁኔታ ከግምት አስገብቶ ኑዛዜ እንዲይደርግ፣ እንዳይለውጥ ወይም እንዳይሽር የከለከለ እንደሆነ ወይም አስቦ ያለ ሟች ፍቃድ የመጨረሻውን ኑዛዜ ያበላሸ፣ እንዳይገኝ ያደረገ፣ ያጠፋ ወይም ጉዳየን በማወቅ በሐሰት ኑዛዜ የተጠቀመ እንደሆነ ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት አንድ ሰው ከጥፋቱ መጠቀም የለበትም ከሚለውን የሕግ መርህ በመነሳት ነው፡፡
ምንጭ
የፍትሐብሔር ሕግ
በይነ መረብ
mr zee
Comments
Be the first to add a comment