የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ሰላም ውድ የቴሌግራም ቻናል አባሎቻችን! በቦሌ ክ/ከተማ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት በተከፈተው ቻናላችን የተለያዩ ሕጎችን እና ሕገ-ነክ ጉዳዮች በማሰራጨት እንገኛለን፡፡ብዙ ሰዎች ቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ከምናሰራጫቸው መረጃዎች ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንክ በቻላችሁት መጠን share በማድረግ ማህበረሳባችን ሕግን በደፈናው ከመፍራት ይልቅ ሕግን በማወቅ ለሕግ ተገዢ ይሆን ዘንድ ብትተባበሩን ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው፡፡
ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ የስራ ቀናት በፌደራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ዙሪያ አንዳንድ ነጥቦችን የማጋራችሁ ይሆናል፡፡ ይህንኑ አዋጅ በ soft copy ለምትፈልጉ ከጽሑፌ ስር አያይዤላችኋለው፡፡
መንግስታዊ አሰራር ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን እንዳለበት
ማናቸውም የመንግስት ባለሥልጣን ኃላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ መሆን እንዳለበት
የአስተዳደር ተቋማት በሰዎች መብቶችና ጥቅሞች ላይ የሚያስከትሉትን ጣልቃ ገብነት በሕግ የሚመራና ለሕግ የሚገዛ መሆን እንዳለበት እና
የአስተዳደር ተቋማት የውሳኔ አሰጣጥና የመመሪያ አወጣጥ መርሆዎችና ሥነ-ሥርዓት እንዲሁም በአስተዳደራዊ ውሳኔዎችና መመሪያዎች ቅር የተሰኘ ሰዉ የውሳኔዎቹንና የመመሪያዎቹን ሕጋዊነት በፍርድ ቤት የሚያስመረምርበት ሥርዓት በመደንገግ አስተዳደራዊ ፍትህን ማስፈን አስፈላጊ መሆኑን፤ ሁላችንም የምንስማማበት ነጥብ ነው፡፡ እነዚህን ነጥቦች ከግብ ለመምታት መጋቢት 29 ቀን 2012 ዓ.ም የፌደራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓትን ለመደንገግ አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ወጥቷል፡፡
የአዋጁን የተፈጻሚነት ወሰን በተመለከተ ይህ አዋጅ በሁሉም የአስተዳደር ተቋማት ላይ ተፈፃሚ ሲሆን በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጉ በሚመሩ የዐቃቤ ሕግ እና የፖሊስ ተግባራት እንዲሁም በመከላከያና፣ የደህንነት ተቋማት ላይ ተፈጻሚ እንደማይሆን የተደነገገ ቢሆንም እነዚህ ተቋማት፣ ከዋና ኃላፊነታቸው በተጓዳኝ ፣ አገልግሎት የመስጠትና የቁጥጥር ሰራዎችን በተመለከተ፣ መመሪያ ሲያወጡ እና አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን ሲወስኑ በዚህ አዋጅ መሰረት እንደሚገዙ አዋጁ አስፍሮልናል።
ይቀጥላል
ሰናይ ዕለተ ሐሙስ! (6/5/2013 ዓ.ም) (ኦምኒኤል)
Comments
Be the first to add a comment