የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
በፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 አንቀጽ 7 መሠረት ማንኛውም ሰው የጥብቅና ፍቃድ የማይሰጠው፡-
1. በዚህ አዋጅ አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ (1) ላይ የተመለከቱትን መስፈርቶች ያላሟላ ከሆነ፤
(ማንኛውም በጥብቅና ሙያ መሰማራት የሚፈልግ ሰው የጥብቅና ፍቃድ ለማግኘት የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡- ሀ) የኢትዮጵያ ዜግነት ያለው ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ፣ ለ) እውቅና ካለው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ቢያንስ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው፣ ሐ) ለመጨረሻ ጊዜ ይሰራበት ከነበረበት ተቋም ድርጅቱን ከመልቀቁ በፊት ባሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በከባድ ዲስፕሊን ጥፋት ያልተቀጣ እና የመልካም ሥነ-ምግባር ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ እና መ/በሕግ ሙያ የሚፈለገውን የሥራ ልምድ ያሟላ እና እንደ አስፈላጊነቱ ፍቃድ ለማግኘት የሚሰጠውን የሙያ መግቢያ ፈተና ያለፈ፡፡ )
2. ታስቦ በሚፈጸምና ከሙያ ሥነ-ምግባር ጉድለት ጋር በተያያዘ ሶስት ዓመትና ከዚያ በላይ ጽኑ እስራት በሚያስቀጣ ወንጀል ተከሶ ጥፋተኛ ከተባለ እና አግባብነት ባለው ሕግ ያልተሰየመ ከሆነ፤
3. በሕግ አገልግሎት እንዳይሰማራ በሕግ ወይም በፍርድ ቤት የተከለከለ ከሆነ ነው፡፡
ኦምኒኤል (ህዳር 30/03/2014 ዓ.ም)
Comments
Be the first to add a comment