👉የኢትዮጵያ የሪል እስቴት ገበያ እንዴት እየሄደ ነው?

💫የሪል እስቴት ገበያ በብዙ ጉዳዮች የሚቃኝ ሲሆን የሪል እስቴት ገበያ በዋነኛነት ከኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጋር ይያያዛል።

⏺ፈጣን እና ተከታታይነት እንቅስቃሴ ካለ የሪል እስቴት ገበያው ይጦዛል።

🚧የዱባይ አየር ሞቃት ነው ከዓመት ውስጥ ለብዙ ወራት የሚጨንቅ ነው በዚያ በረሃና የሚጨንቅ አየር ማን ይኖራል? ብዙ ሰው! ለምን? ሥራ አለኣ! ንግድ አለኣ!

💫ንግድና ሥራ ባይኖር ማንም ዱባይ ላይ አይቀመጥም። የዱባይ ገዥዎች ግን ነቄ አይደሉ? ከሌላው ዓለም ሰው እንዲመጣ አደረጉ። ለዚህ መሳቢያነት ታክሱን ዜሮ አደረጉ።

⏺በዚህ ምክንያት የዱባይ ገበያ ሁሌም እንደቆመ ነው። አይበርድም! የሪል እስቴት ገበያውም ያንን ተከትሎ እንደጎነ ነው። ደስ የሚለው የኛም ሀገር ሰዎች በዚያ የዱባይ ገበያ ላይ ተቋዳሽ ሆነዋል።
ረምዚን ሪል እስቴት እና ብሩክ ሪል እስቴትን ማየት ነው።

❇️እነ The First Group ገበያ ፍለጋ እዚህ ሲመጡ የኛዎቹም እዚያ ሄደው ገበያውን እየተሻሙ ነው። እንዲህ ነው ጨዋታ። በራስ ሜዳ ብቻ መጫወት ለብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድኑም አልበጀም።

⏺ንግድ ዝም ብሎ አይጦፍም። የተለኮሰ እሳት እንኳ ዝም ብሎ አይነድም። ነዳጅ ወይም ማገዶ እና አየር ይፈልጋል። ማራገብ ያስፈልጋል።

🏷የሀገራችን የሪል እስቴት ገበያ ኢኮኖሚውን ተከታይ ነው። የኢትዮጵያ ሪል እስቴት ገበያ እንዲጦፍ ኢኮኖሚው ሊነቃቃ ይገባል።

ሰላም እና የኢኮኖሚ መነቃቃት ያለባቸው የክልል ከተሞች ላይ የሪል እስቴት ገበያ መጦፉ የማይቀር ነው። ኢኮኖሚው የጦፈው የት ክልል ላይ ይመስላችኋል? መሃል ሜዳው ሲወጠር ወደ ክንፍ አተኩሩ! ይል ነበር የድሮ የኳስ አሰልጣኛችን።
ďťż
📜ለመሆኑ ድሬ/አቡሴራ ላይ የሚገነባው የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ምን ላይ ደርሷል?

⏺አዲስ አበባ ላይ ብዙ ክፍት መሬት አለ። የአዲስ አበባ ዋጋ እየወረደ ነው። ቶሎ የሚነሳም አይመስልም። እዋይ! ቤታችን። ውሃ በላው!

ለማንኛውም ፈጣን የስትራተጂ ለውጥና ማስተካከያ ያስፈልጋል።

Via ኢንፍራኮን ሚዲያ


@etconp

Comments

Be the first to add a comment