👉የኢትዮጵያ መንገዶች ባለፉት ስምንት ዓመታት

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (ኢ.መ.አ) ክልሎችን እርስ በርስ የሚያገናኝና ሀገራዊ የንግድ  ኮሪደሮችን የሚያጠናክር ጠንካራ የፌዴራል የመንገድ መረብ የመዘርጋት ተልዕኮውን ወደ ተግባር በመለወጥ ረገድ ያስመዘገበው አሀዛዊ መረጃ በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን ያሳያል።

▪️  በ2010 ዓ.ም የነበረው የ126,773 ኪሎ ሜትር አጠቃላይ የመንገድ ሽፋን በ2018 ዓ.ም አጋማሽ ወደ 180,232 ኪሎ ሜትር በማደጉ፣ ከ53 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ አዲስ መንገድ ለሀገሪቱ ተጨምሯል።

▪️ የመንገድ ጥግግቱ በየ1000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ከ115.2 ወደ 157 ኪሎ ሜትር አድጓል።

▪️ ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ ብቻ 182  ፕሮጀክቶች ወደ ግንባታ እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን፣ 71 ግዙፍ ፕሮጀክቶች ግንባታቸው ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆነዋል።

▪️ ተቋሙ የመንገድ ጥራትን ከመጠበቅ አንጻርም 80,037 ኪሎ ሜትር መደበኛ ጥገና እና 3,035 ኪሎ ሜትር ከባድ ጥገና በማከናወን የሀገሪቱን የመንገድ ሀብት የመንከባከብ ስራ በትኩረት ሰርቷል።

▪️  የውጤቱ ሌላኛው ማሳያ ሀገራችንን የንግድና የኢንዱስትሪ ማዕከል የሚያደርጉ ግዙፍ የፍጥነት መንገዶች እውን መሆናቸው ነው።

▪️ከለውጡ በፊት የነበረው 84.7 ኪ.ሜ የሚረዝመው የአዲስ አበባ-አዳማ የፍጥነት መንገድ ብቻ ሲሆን፣ ዛሬ ግን የሞጆ-መቂ-ባቱ-አርሲ ነገሌ (151 ኪ.ሜ) እና የድሬዳዋ-ደዋሌ (220 ኪ.ሜ) የፍጥነት መንገዶች ተጠናቅቀው ለአገልግሎት በቅተዋል።

▪️  ከዚህ በተጨማሪ ተቋሙ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ፣ ጅማ፣ ደብረ ማርቆስ እና ነቀምቴ የሚዘልቁ አራት አዳዲስ የፍጥነት መንገዶችን ለመገንባት የአዋጭነት ጥናት እያጠናቀቀ ሲሆን፣ ይህም ኢትዮጵያን በ10 ዓመታት ውስጥ የ1,600 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ ባለቤት ለማድረግ ለተያዘው ግብ ትልቅ እርምጃ ነው።

▪️  ሌላኛው ትልቅ ስኬት ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያገናኙ ግዙፍ መንገዶች እውን መሆናቸው ነው። 

▪️ ተቋማዊ አደረጃጀትን በማዘመንና ዘመናዊ አሰራርን በመዘርጋት ረገድም በለውጡ ማግስት ሰፊ ስራዎች ተከናውነዋል።

▪️ ቀደም ሲል ተነጥለው የነበሩ የመንገድ ጥገና ዲስትሪክቶችና ሴክሽኖች ወደ ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር እንዲመለሱ ተደርጓል።

▪️በተጨማሪም በሀገሪቱ በተለያዩ ክፍሎች  የግንባታ ፕሮጀክቶች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቶች ተከፍተው ሾል እንዲጀምሩ በመደረጉ፣ የፕሮጀክቶች ክትትልና ድጋፍ በመንገድ ግንባታው ስፍራ ቅርብ እንዲሆኑ አስችሏል።

▪️  የመንገድ ሀብቱን ለመጠበቅና የከባድ ተሽከርካሪዎችን ጫና ለመቆጣጠር የሚረዱ የሚዛን ጣቢያዎች ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በማስፋፋት እና ያሉትን ዲጂታላይዝ እንዲሆኑ ተደርገዋል።

▪️ ይህ የዲጂታላይዜሽን ስራ የተሽከርካሪዎችን ክብደት ከሰው እጅ ንክኪ ነጻ በሆነ መልኩ በመመዝገብ፣ የአሰራር ግልጽነትን በማስፈንና የመንገድ ብልሽትን በመቀነስ ረገድ የላቀ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

▪️  በመንገድ ምርምር ረገድም የተቋሙን የምርምርና ላቦራቶሪ ማዕከል አቅም በማሳደግ የመንገድ ግንባታ ግብአቶችን ጥራት በሳይንሳዊ መንገድ ለመፈተሽ የሚያስችሉ ስራዎች ተሰርተዋል።

▪️ የዘርፉን አቅም ለመገንባትም በቢሊዮን የሚቆጠር ብር ወጪ የተደረገባቸው በርካታ ዘመናዊ ለመንገድ ግንባታ የሚውሉ ማሽነሪዎች ግዢ መፈጸሙ  እና ሌሎችም በርካታ ተግባራት ተከናውነውል።

Via ERA

@etconp

1 comment

እነዚህ ቁጥራዊ መረጃዎች በትክክል መገምገም አለባቸው። ሌላው የተጀሩ ፕሮጀክቶች አለማለቅ ብሎም ሙሉ ለሙሉ መቋረት መሠረታዊ ችግሮች ናቸው። ለምሳሌ እኔ በ2012 ዓ.ም በ2012 ዓም የ4ተኛ አመት ተማሪ በነበርኩበት አፓረንት የወጣሁበት ጣርማበር መላሌ ሠፌድ ሜዳ ፕሮጀክት የቆረጣ ስራ ፣የሰብ ግሬድ እና ሰብ ቤዝ ስራ ላይ የነበረ እና የ36 ወር የኮንትራት ጊዜ እና የ1.9 ቢሊዮን ብር በጀት ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት በቦታው ላይ ምንም ነገር የለም። በዚህም ከፍተኛ ሰቆቃ እየደረሠ ነው።