👉የግንባታ ጨረታ ግምገማ ውጤት ለተጫራቾች በደብዳቤ ሲገለጽ፤ የጨረታው ግልፅነት፣ ፍትሃዊነት እና ተወዳዳሪነት እንዲረጋገጥ የሚከተሉትን መሰረታዊ ነጥቦች ማካተት ይኖርበታል።

🌟ለአሸናፊው ተጫራች የሚላክ ደብዳቤ የሚከተሉትን መያዝ አለበት፡-

⏺የውሳኔው መግለጫ፡ የቴክኒክና የፋይናንስ ሃሳቡ አሸናፊ መሆኑን የሚያረጋግጥ።

⏺የውል ጠቅላላ ዋጋ፡ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ (በቁጥር እና በፊደል፣ እንዲሁም ታክስን ጨምሮ)።

⏺ቀጣይ እርምጃዎች፡ ውል ለመዋዋል ወይም ውል ማስከበሪያ (Performance Bond) የሚጠበቁበትን ቅድመ-ሁኔታዎችና የጊዜ ገደብ።

🔆ለተሸናፊ ተጫራቾች የሚላክ ደብዳቤ የሚከተሉትን መያዝ አለበት፡-

▶️የውሳኔው መግለጫ፡ በጨረታው ማሸነፍ አለመቻላቸውን በግልፅ የሚያመላክት።

▶️አንዳንድ ግዥ ፈፃሚ መ/ቤቶች የውሳኔ መግለጫ አባሪ ያልተደረገበትን ነጠላ ደብዳቤ ይሰጣሉ፣ ይህ ስልተት ነው።

▶️ያለፉበት ደረጃ ማጠቃለያ፡ የቴክኒክ ውጤታቸው (Responsive አለመሆናቸው) ወይም የፋይናንስ ደረጃቸው።

▶️የውድድር ደረጃ መግለጫ(Rank): እያንዳንዱ ተጫራች በቴክኒክና በፋይናንስ ግምገማ ያገኘውን ውጤት/ደረጃ (ለምሳሌ፡- 1ኛ፣ 2ኛ፣ ወዘተ) በመጥቀስ ተወዳዳሪነቱ እንዲረጋገጥ ማድረግ ይኖርበታል።

⬆️አንዳንድ ግዥ ፈፃሚ መ/ቤቶች የተጫራቾችን ደረጃ የማይገልጽ ደብዳቤ ይሰጣሉ፤ ይህ ስህተት ነው።

⬆️የተጫራቾች ደረጃ(1ኛ፣ 2ኛ፣ 3ኛ፣ ወዘተ) በግልጽ መታወቅ አለበት።

⬆️አሸናፊው የተመረጠበት መስፈርት እና የደረጃ ሰንጠረዥ (Evaluation Matrix) የግድ ለተጫራቾች ሊሰጥ ይገባል።

⬆️የተሸነፉበት ምክንያት፡ ተጫራቾች ያልተሳኩበትን ዝርዝር ምክንያት(የተሻለ ተወዳዳሪ ዋጋ በመኖሩ ወዘተ.)።

⬆️የአሸናፊው ማንነት፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነውን ተቋራች ስምና አሸናፊ የሆነበትን ዋጋ።

⬆️አሸናፊ የሆነውን ተጫራች ሙሉ ስም እና አሸናፊ ለመሆን ያስቻለውን አጠቃላይ የውል ዋጋ(ከግብር ጋር) መግለጽ ይኖርበታል።

⬆️የቅሬታ አቀራረብ መብትና ጊዜ፡ ስለ ውጤቱ ቅሬታ (Complaint) ለማቅረብ የሚችሉበትን አሰራር እና የተፈቀደውን የስራ ቀናት ገደብ።

⬆️የጨረታ ዋጋ ማብራሪያ Value for Money: የአሸናፊው ድርጅት ዋጋ ከመንግስት ወይም ከድርጅቱ ከተያዘው በጀት እና ከገበያ ዋጋ ጋር ተመጣጣኝ መሆኑን የሚያሳይ አጭር ማብራሪያ ማካተት ይኖርበታል።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment