👉በኮንስትራክሽን ዘርፍ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መያዝ አስገዳጅ ሊሆን ነው

🪧በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ለሚሳተፉ ባለሙያዎች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መያዝ አስገዳጅ እንደሚሆን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ በኮንስትራክሽን ዘርፉ ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ያሉ ባለሙያዎች በአግባቡ ሰልጥነው፣ ህጋዊ የሰርቲፊኬሽን ስርዓት ውስጥ አልፈው ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

የስልጠና፣ የምዘና እና የሰርቲፊኬሽን ስርዓት ተደራሽና ውጤታማ ለማድረግ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ማዕከላትን በበላይነት ከሚያስተዳድረው ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

ይህንን አሰራር ደረጃ በደረጃ በማሳደግ ሰርተፊኬት የሌላቸው ባለሙያዎች በየትኛውም ደረጃ በሚገኙ የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ እንዳይሳተፉ እንደሚደረግና ሙሉ በሙሉ አስገዳጅ እንደሚሆን አስገንዝበዋል።

ህጉን ሙሉ በሙሉ አስገዳጅ አድርጎ ወደ ትግበራ ከማስገባት አስቀድሞ መከናወን ያለባቸው የቅድመ ሁኔታ ስራዎች ተጠናቀው ምቹ ሁኔታ መፈጠር እንዳለበት አመላክተዋል።

የሰርቲፊኬሽን ስርዓቱን አስገዳጅ የማድረግ ሂደቱ ዓመታትን ሊፈጅ የሚችል ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን የተግባር እንቅስቃሴው ተጀምሯል ብለዋል።

Via የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

@etconp

Comments

Be the first to add a comment