የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ
Rent Control and Administration Proclamation
በአዲስ አበባ ከተማ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረው የመኖሪያ ቤት አከራይ ተከራይ ውል እድሳት ጋር ተያይዞ በመነሳት ላይ ያለው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ፤
ይህ አዋጅ ተፈፃሚ የሚሆነው ተጠሪነታቸው ለክልል በሆኑ ከተሞች፣ በአዲስ አበባ እና በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ላይ በሚፈፀም የመኖሪያ ቤት ኪራይ ላይ ሲሆን ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ አዋጁ በሌሎች ከተሞች ላይ ተፈፃሚ ሊሆን ስለሚችልበት ሁኔታ ክልሎች ነባራዊ ሁኔታውን እያዩ እንደሚወስኑ አዋጁ ያስቀምጣል።
በተጨማሪም አዋጁ ተፈፃሚ ከሚሆንበት ሁኔታ ውጪ ተፈፃሚ የማይሆንበት ሁኔታ ተመለከቷል።
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል የኪራይ ዘመኑ ሳይጠናቀቅ በአከራዩና ተከራዩ ስምምነት፣ ተከራይ ቤቱን መልቀቅ ሲፈልግ የሁለት ወር የቅድሚያ ማስታወቂያ በመስጠት ወይም የቤት ባለቤትነት በሕጋዊ መንገድ ለሌላ ሰው ሲተላለፍ የ6 ወር ማስጠንቀቂያ በመስጠት ሊቋረጥ ይችላል።
እነኚህ ውሉ በማስጠንቀቂያ የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች ሲሆኑ ውሉ ያለማስጠንቀቂያ የሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች ደግሞ በአንቀጽ 16 ስር ተዘርዝረው ይገኛሉ።
@etconp