👉አዲስ አበባ ውስጥ 4 አዳዲስ ሞሎች በ2019 ዓ.ም. ሥራ ሊጀምሩ ይጠበቃል

💫ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቱሪዝም ዘርፍ ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያ፣ በአዲስ አበባ እየተገነቡ ካሉት ትላልቅ የንግድ ማዕከላት (ሞሎች) መካከል 3 እስከ 4 የሚደርሱ ሞሎች በሚቀጥለው ዓመት ሥራ እንደሚጀምሩ ገልጸዋል።

🚧እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ ቱሪዝም የሚያድገው ጎብኚዎች የሚጎበኙበት ቦታ ብቻ ሳይሆን የግብይት፣ የመዝናኛ፣ የምግብ፣ የባህል ውጤቶች እና የገበያ አገልግሎቶች ሲገኙ ነው።

💫አዲሶቹ ሞሎች ሲጠናቀቁ፣

✅ የንግድ እና የቱሪዝም እንቅስቃሴን ያበረታታሉ፣

✅ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ይፈጥራሉ፣

✅ የመዝናኛና የግብይት አማራጮችን ያሰፋሉ፣

✅ አዲስ አበባን በአፍሪካ ዘመናዊ የንግድ ማዕከላት ካሏቸው ከተሞች ተርታ ለማሰለፍ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ተብሏል።

📌 የኢትዮ ኮን እይታ የእነዚህ ሞሎች መገንባት ለኮንስትራክሽን፣ ለሪል እስቴት፣ ለንግድ እና ለቱሪዝም ዘርፎች ጉልህ እድል የሚፈጥር ሲሆን፣ በመዲናዋ የዘመናዊ የንግድ መሠረተ ልማት እድገትን የሚያፋጥን እርምጃ ነው።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment