👉“የኮንስትራክሽን አሠሪዎች በየዓመቱ ተመዝነው ደረጃ የሚያገኙበት ሥርዓት ይዘረጋል” - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
💫በቀጣይ ጊዜያት ተቋራጮችና አማካሪዎች ብቻ ሳይሆኑ አሠሪዎችም በየዓመቱ ተመዝነው ደረጃ የሚያገኙበት ሥርዓት ይዘረጋል ሲሉ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ኢኒሸቲቭ ትናንት ይፋ ሲደረግ እንዳስታወቁት፤ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሶስት ሺህ ዓመታት በላይ ታሪክ አለው።
በዘርፉ አሁን ላይ ያለው እውነታ ከሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ታሪክ ጋር የተጣላ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህንን የዘርፉን ስብራት ለመጠገን መንግስት ጨርሶ የመጀመር እና ፕሮጀክቶችን በጊዜ ገንብቶ የማጠናቀቅ ባህልን ለዘርፉ እያስተዋወቀ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
በዚህም ቀንና ሌሊት የመስራት ልማድ፣ ውጤታማ የፕሮጀክት ክትትል እና ገንዘብን ለታለመለት ዓላማ ማዋል ተችሏል ብለዋል።
ከእንግዲህ ተቋራጮችና አማካሪዎች ብቻ ሳይሆኑ አሠሪዎችም በየዓመቱ ተመዝነው ደረጃ የሚያገኙበት ሥርዓት ይዘረጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የአፈፃጸም ጉድለት ከታየባቸው ተጠያቂ እንደሚሆኑና ሁሉም ባለድርሻ አካላት አፈፃጸማቸውን የሚመጥን እውቅና እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል፡፡
ይህም ዘርፉን ውጤታማ በማድረግ በአህጉር እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርገው ይሆናል ብለዋል፡፡
Via ጋዜጣ ፕላስ
@etconp