👉ኢንሰቲትዩቱ ዘርፉ በቴክኖሎጂ ማስደገፍ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

▶️ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ተወዳዳሪ እንድሆኑ ለማስቻል የዘርፉን ቴክኖሎጂዎች በተሻለ መልኩ  በመምረጥ፣ በመገምግምና በማሸጋገር  እንድሁም  ቴክኖሎጂውን በተሻለ መልኩ  በማሰራጨት በኢንዱስትሪው ጥቅም ላይ እንድውሉ እና ይህኑ የሚደግፍ መመሪያዎችና አሰራር ሥርዓቶችን ለመቅጽ  የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ  ከRising Hongfa ኃላፊነቱ የተወሰነ አ.ማ  ጋር ተፈራርሟል፡፡

📝📓በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት በኢንስቲትዩቱ የአቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ቅድስት ማሞ ሲሆኑ፣ ባደረጉት ንግግርም ኢንስቲትዩቱ የዘርፉን ተዋናዮች አቅም ከመገንባት፣ ችግር ፈችና ለፖሊሲ ግብዓትነት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ጥናትና ምርምሮችን  ከማድረግ በተጨማሪ ለዘርፉ ተወዳዳሪነትና ውጤታማነት ፋይዳ ያላቸውን ቴክኖሎጂዎችን በመለዬትና ውጤታማነታቸውን በማረጋገጥ በኢንዱስትሪው ጥቅም ላይ እንድውሉ  ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ሲሰራ መቆየቱን ተናግሯል፡፡

✴️ ይህም የመግባቢያ ሰነድ ይህንኑ በተሻለና በተቀናጀ መልኩ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ኢንዱስትሪው በማሸጋገር ዘርፋ በማህበረ-ኢኮኖሚ ዕድገት መጫወት የሚገባውን ሚና እንድጫወት አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡

✴️ አክስዮን ማህበሩን  በመወከል ንግግር ያደረጉት አቶ አመንቴ ዳድ ሲሆኑ፣ በንግግራቸውም አክስዮን ማኅበሩ  በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የአክስዮን ድርሻነት የተቋቋመ መሆኑን በማስገንዘብ፣ የተቋቋመበት ዓላማም ኢንዱስትሪው የሚጠቀማቸውን ከፍተኛ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን  ለኢንዱስተሪው የማስተዋወቅና የማሸጋገር እንድሁም በዘርፉ ጥቅም ላይ እንድውሉ ዓላማ አድርጎ የሚሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ከኢንስቲትዩቱ ጋር የተደረገው የመግባቢያ ስምምነት ፊርማ ቴክኖሎጂዎችን በተደራጀና ቀጣነት ባለው መልኩ  እንድሸጋገሩ ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

✴️ በዚህ መግባቢያ ሰነድ ላይ እንደተገለጸው ኢንስቲትዩቱ ቴክኖሎጂዎችን ከመምረጥ ቴክኖሎጂዎቹን፣ ከማሸጋገርናማሰራጨት በስልጠና ዎርክሾፖችን በማዘጋጀት፣ የኢንዱስትሪው ተዋናዮች የግንዛቤ የማስጨበጥ እና በመሳሰሉት ረገድ ተቋማዊና ቴክንካዊ ድጋፍ የማድርግ እንድሁም Rising Hongfa ኃላፊነቱ የተወሰነ አ.ማ  በበኩሉ የቴክኖሎጂ ማሸጋገሩንና ማሰራጨቱን በገንዘብና በቴክንክ የመደገፍ፣ በኢንዱስትሪው ቴክኖሎጂዎቹን የማላመድ፣ የክትትልና የመቆጣጠር እና የመሳሰሉት ኃላፊነቶች ተጥሎበታል፡፡

✴️ በአጠቃላይ ሁለቱም ተቋማት ለኢንዱስትሪው ተወዳዳሪነትና ውጤታማነት የበኩላቸውን ሚና  በጋራ ለመወጣት የተቀናጁ መሆናቸውን በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ገለጻ ለመረዳት  ተችሏል፡፡

@etconp

Comments

Be the first to add a comment