የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ይህንን ያውቃሉ
❓
❓
የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ በወረዳ ጽሕፈት ቤቶቹ የሚሰጣቸውን የኩነት (የልደት፣ ጋብቻ፣ ፍቺ፣ ሞትና ጉዲፈቻ) ማስረጃዎችን የማረጋገጥ አገልግሎት ለማግኘት ተገልጋዮች ይዘው መቅረብ የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችንና ደጋፊ ሰነዶችን እንደሚከተለው ያሳውቃል።
ለእያንዳንዱ አገልግሎት የሚያስፈልጉ ልዩ ቅድመ ሁኔታዎች
1. የልደት ሰርተፍኬት ለማረጋገጥ
ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ፦ በወረዳ ደረጃ የተመዘገበ የልደት ማስረጃ
አገልግሎቱ የሚሰጠው ከሁለቱ አንዱ ወላጅ በአካል ሲገኝ ነው (የወላጆች የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ያስፈልጋል)።
ምዝገባው በሞግዚትነት ከሆነ የፍርድ ቤት የሞግዚትነት ውሳኔ ሰነድ መቅረብ አለበት።
ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ፦ ባለጉዳዩ በአካል መቅረብ አለበት። በአካል መቅረብ ካልቻለ፣ ጉዳዩን የሚገልጽ ልዩ ውክልና ከወካይና ተወካይ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
2. የጋብቻ ማስረጃ ለማረጋገጥ
በክፍለ ከተማ ወይም በወረዳ ደረጃ የተመዘገበ የጋብቻ ማስረጃ መያዝ።
ለግልባጭ ወይም ለእርማት አገልግሎት፦ የተጋቢዎች ሁለት ሁለት (2) ጉርድ ፎቶግራፍ።
በውክልና የሚጠየቅ ከሆነ (ለእርማት፣ ዕድሳትና ግልባጭ)፦ ባልና ሚስት ጉዳዩን በግልጽ የሚያሳይ ውክልና፣ የወካዮች እና የተወካይ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት ወይም የታደሰ የመኖሪያ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።
3. የፍቺ ማስረጃ ለማረጋገጥ
በክፍለ ከተማ ወይም በወረዳ ደረጃ የተመዘገበ የፍቺ ማስረጃ
የህግ አስገዳጅነቱ የተረጋገጠ የፍርድ ቤት የፍቺ ውሳኔ ሰነድ መቅረብ አለበት።
4. የጉዲፈቻ ሰርተፍኬት ለማረጋገጥ
በወረዳ የተመዘገበ የጉዲፈቻ ሰርተፍኬት እና የፍርድ ቤት ውሳኔ ሰነድ
ጉዲፈቻ አድራጊዎች የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት በመያዝ በአካል መቅረብ አለባቸው።
ጉዳዩ በውክልና ከሆነ፣ይህንኑ የሚያስረዳ ልዩ ውክልና መቅረብ አለበት።
5. የሞት ማስረጃ ለማረጋገጥ
በወረዳ ደረጃ የተመዘገበ የሞት ማስረጃ የማረጋገጥ አገልግሎት ለማግኘት
ከሟች ጋር አብሮ ይኖር የነበረ ሰው፣ እርሱ ከሌለ የሟች የስጋ ወይም የጋብቻ ዘመዶች፣ እነዚህም ከሌሉ የቅርብ ጎረቤት ወይም ስለሟቹ መሞት የሚያውቅ ማንኛውም ሰው የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት በማቅረብ ማስመዝገብና ማረጋገጥ ይችላል።
ሟች የውጭ ሀገር ዜጋ ከሆነ ከሆስፒታል የተሰጠ የማሳወቂያ ወረቀት መቅረብ አለበት።
ማሳሰቢያ፡- ለሁሉም ከላይ ለተዘረዘሩት የኩነት አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስፈልግ ደጋፊ ሰነድ
• የታደሰ ብሔራዊ መታወቂያ / የታደሰ ፓስፖርት / የትውልደ ኢትዮጵያ የውጭ ዜግነት መታወቂያ (የቢጫ ካርድ)።
• ከዝቅተኛው አስተዳደር ጽ/ቤት መደበኛ ነዋሪነቱን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ / የስደተኛነት ማስረጃ / የመኖሪያ ፈቃድ።
• ከሚሰራበት መስሪያ ቤት ባልደረባነቱንና ዜግነቱን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ከመስሪያ ቤቱ መታወቂያ ጋር / የመከላከያ ሰራዊት ከሆነ የመከላከያ ሰራዊት መታወቂያ መያዝ
• የጠፋ ሰርተፍኬት ግልባጭ ለመውሰድ፦ ከፖሊስ የተሰጠ የጠፋ ሰነድ ማረጋገጫ ማቅረብ ግዴታ ነው።
• ከወረዳ የመጡ ማስረጃዎች፦ ከወረዳው ስለመውጣታቸው የሚገልጽ ማረጋገጫ ደብዳቤ ያስፈልጋቸዋል።
• ከክፍለ ከተማ የመጡ ማስረጃዎች፦ ከሰነዱ በስተጀርባ የማረጋገጫ ማህተም ማረፍ ይኖርበታል።
• ከውጭ ሀገር የሚመጣ ውክልና፦ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በፌደራል ሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ መረጋገጥ አለበት።
=====================
Comments
Be the first to add a comment