አማራጭ የመንገድ ጥቆማ
ከጎሮ - ኮዬ ፈቼ - ቱሉ ድምቱ አደባባይ በሚወስደው መንገድ ላይ የኮሪደር ልማት እየተከናወነ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም ምክንያት በመሬት ውስጥ ለሚቀበር የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ሲባል፤ ከኮዬ ወደ ጎሮ አደባባይ የሚወስደው አስፋልት መንገድ ተቆርጦ እየተሰራ መሆኑ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም በተላለፈው ማስታወቂያ መገለፁ ይታወሳል፡፡
በመሆኑም በሥፍራው እየተካሄደ ባለው የግንባታ ሥራ ምክንያት ከነገ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ እሁድ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ፤ ከጎሮ አደባባይ - ኮዬ ፈቼ የሚወስደው መንገድ በከፊል ለትራፊክ ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡ ስለሆነም፡-
• ከኮዬ ፈቼ ወደ ጎሮ አደባባይ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች በቡልቡላ በኩል - ቦሌ ኤርፖርት - ጎሮ አደባባይ የሚወስደውን አዲሱን መንገድ እንዲጠቀሙ፤
• በተመሳሳይም፤ ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ ፈቼ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች፣ የትራፊክ መጨናነቅ ሁኔታን ለመቀነስና ጊዜ ለመቆጠብ፤ ከጎሮ - በቦሌ ኤርፖርት አዲሱ መንገድ በመጠቀም በቡልቡላ በኩል ወደ ኮዬ አደባባይ መጓዝ የሚቻል መሆኑን ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ይገልፃል፡፡
የተሻለ መንገድ፣ ለተሻለች አዲስ አበባ፤
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን
@ETCONP