👉ለጨረታ ማስከበሪያ ከመድን የሚቀርቡ ዋስትናዎች (Conditional Bond) ከዚህ በኋላ ተቀባይነት አይኖራቸውም። ሾል ተቋራጮች ለውል ማስከበሪያ ከመድን የሚያቀርቡት ዋስትና Unconditional  መሆን ይጠበቅበታል።

- በነባሩ የፌደራል ግዥ መመሪያ በግንባታ ስራ ለተሰማሩ የሃገር ውስጥ ስራ ተቋራጮች በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ የመድን ዋስትና (Conditional Insurance Bonds) ለጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የነበረው ቢሆንም አዲሱ መመሪያ ይህንን አማራጭ አላካተተም።

- ለውል ማስከበሪያ ደግሞ  ከአገር ውስጥ የግንባታ ዘርፍ ሼል ተቋራጮች ወይም መድሐኒት እና የሕክምና መሣሪያዎች አምራች ድርጅቶች ለሚፈጸም ግዥ ከታወቀ የመድን ድርጅት የሚቀርብ በሁኔታ ላይ ተመሠረተ የመድን ዋስትና ቢያቀርቡ ተቀባይነት የነበረው ቢሆንም በአዲሱ የግዥ መመሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ መሆን እንዳለበት ተመላክቷል።

N.B. የሃገር ውስጥ መድን ድርጅቶች በብሄራዊ ባንክ በኩል በተሰጣቸው መመሪያ መሰረት በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (Unconditional) መስጠት የማይችሉ ከመሆኑ አንጻር ይህ እንዴት ተፈጻሚ ሊሆን እንደሚችል ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው።

- የአገር ውስጥ ስራ ተቋራጮች እንዲሁም የመድሀኒት እና ሕክምና መሳሪያ አምራች ኢንዱስትሪዎች በሁኔታ ላይ የተመሰረተ (conditional) የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና (Advance Payment Guarantee) ከታወቀ የመድን ድርጅት ሊያቀርቡ እንደሚችሉ የሚገልፀው አንቀፅ ባለበት ፀንቷል።

🏷የ YouTube ገፃችን ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp

Comments

Be the first to add a comment