የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ!
የኢፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 27 ቀን 2016 ባፀደቀው የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 አንቀጽ-11 መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ወደ አገር የሚገቡ ዕቃዎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ናቸው፡-
ሀ/ በቪዬና የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ኮንቬንሽን ሚሲዮኖች፣ ዲፕሎማቶች ወይም የኩንሱላር ጽ/ቤቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ እስከሆኑ ድረስ እነዚህ ሚሲዮኖች፣ ዲፕሎማቶች ወይም የኩንሱላር ጽ/ቤቶች ወደ አገር የሚያስገቧቸው ዕቃዎች፡
ለ/ በዓለም ዐቀፍ ስምምነት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የተደረጉ ዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች ወደአገር የሚያስገቧቸው ዕቃዎች ፤
ሐ/ በፋይናንስ፣ በቴክኒክ፣ በሰብዓዊ ዕረዳታ ወይም በአስተዳደር ድጋፍ የዓለም አቀፍ ስምምነት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ እስከተደረገ ድረስ የውጭ አገር መንግስት ወደ አገር የሚያስገባቸው ዕቃዎች፣
መ/ በጉምሩክ ደንብ ከጉምሩክ ቀረጥ ነጻ እስከተደረገ ድረስ መንገደኛው ይዞት የሚመጣ የግል መገልገያ እቃ፣
ሠ/ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ ከሚወስነው እስካልበለጠ ድረስ ተመላሾች ወደ አገር የሚያስገቧቸው ዕቃዎች፣
ረ/ ወደአገር የሚገባ ለግብርና ሥራ ብቻ የሚውል ምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያ፣ የተባይ ማጥፊያ፣ የአረም ማጥፊያ ወይም የፈንገስ ማጥፊያ፣
ሰ/ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚቀርብ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ ወርቅ፣
ሸ/ የውሃ ማከሚያ፣ አጎበር፣ የህክምና መገልገያ፣ እና የህክምና መሣሪያ፣
ቀ/ በአባሪ-2 ትርጉም የተሰጠው ወደ ሀገር የሚገባ በሐኪም የሚታዘዝ መድኃኒት፣
በ/ በሚኒስትሮች ምክርቤት የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብ ቁጥር-517/2014 በተደነገገው መሰረት ኢንቨስተሮች ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆነው ወደአገር የሚያስገቡት እቃ፣
ተ/ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ ከጉምሩክ ቀረጥ ነጻ ሆነው ወደ አገር እንዲገቡ የተፈቀዱ የካፒታል እቃዎች፣
ቸ/ በጉምሩክ ታሪፍ ደንብ ከጉምሩክ ቀረጥና ከማናቸውም ታክስ ነጻ የሆኑ ያልተመደቡ ወደ አገር የሚገቡ እቃዎች፣
ኀ/ አምቡላንስ እና የእሳት አደጋ ተሸከርካሪዎችና መሳሪያዎች ወደ አገር ማስገባት፣ እና
ነ/ ሚኒስቴሩ በሚያቀርበው ሃሳብ መሰረት በጠቅላይ ሚኒሰትር ጽ/ቤት ከታክሱ ነፃ የሚደረጉ እቃዎች
Comments
Be the first to add a comment