የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ጤና ይስጥልኝ
ግለሰቦች እርስ በ'ርስ የሚያጋጥሟቸውን አለመግባባቶችን በፍ/ቤት አስቀርበው ውሣኔ የማግኘት መብት ያላቸው መሆኑ እንደለ ሆኖ፤ ጉዳያቸውን ሕግ በግልጽ እስካልከለከለ ድረስ በሚመርጡት (በሚመርጧቸው) ሽማግሌዎች ታይቶ ውሣኔ የማሰጠት መብትም ያላቸውና ይህም ደግሞ በብዙ መልኩ (ከጊዜም ከገንዘብም፣ ለሁለቱም ካለማስከፋት አንጻር---) የሚበረታታና በሀገራችን በኢትዮጵያም ይህ ተግባር ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ሲከናወን የነበረና አሁንም የሚከናወን ሲሆን ስለዚሁ ጉዳይም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 3307 እስከ 3346 እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 315 እስከ 319 እና ከቁጥር 350-357 ከተደነገጉት ላይ በመነሳት በሽምግልና የተሰጠን ስለማስፈጸም የሚከተለውን አቀረብን፡-
መልካም ምንባብ፡-
በፍ/ብሔር ሕግ ቁጥር 3131 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ስለተመለከተው የአስተዳደር መሥሪያ ቤቶች የሚያደርጓቸው ውሎች ለግልግል ዳኝነት የማይቀርብ ሆኖ በሌለው በሽምግልና ታይቶ ውሣኔ የተሰጠበትን ግን በጉዳዩ ላይ ቅሬታ ያለው ወገን ይግባኝ ሊያቀርብበት የሚችልበት መሆኑ እና እንደዚሁም ውሣኔው እንዲፈጸም ለመደበኛው ፍ/ቤት ቀርቦ ሊፈጽም እንደሚችል በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚው ችሎት በስ/መ/ቁጥር 27574 አስገዳጅ ውሣኔ የተሰጠበት መሆኑን ግንዛቤ እንያዝበት ፡፡
መልካም ቀን
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ !!!
ታህሳስ 13/2014ዓ.ም
ደረጀ ማርቆስ
Comments
Be the first to add a comment