✿
ጥያቄ |[
የስፖርት ውድድሮችን (ግጥሚያዎችን) የመመልከት ብይን ]|
▢
መልስ ፦ የፈትዋ ኮሚቴ (اللجنة الدائمة):• በገንዘብ ወይም መሰል ሽልማቶች ላይ የተመሰረቱ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ቁማር በመሆናቸው ምክንያት የተከለከሉ (ሀራም) ናቸው። ምክንያቱም በሸሪዓው ከተፈቀዱት (እንደ ፈረስ ውድድር፣ የግመል ውድድር እና የውርወራ/ቀስት ውድድር) ውጪ በውድድር ላይ ክፍያ ወይም ዋጋ መውሰድ አይፈቀድም። በዚህም መሰረት፣ ውድድሩ በሽልማት (በገንዘብ) ላይ የተመሰረተ መሆኑን እያወቀ በቦታው መገኘትም ሆነ መመልከት የተከለከለ ነው፤ ምክንያቱም በቦታው መገኘቱ ድርጊቱን እንደማጽደቅ (እንደመቀበል) ይቆጠራል።
• ነገር ግን ጨዋታው ያለ ምንም ክፍያ (ሽልማት) ከሆነ፣ አላህ ግዴታ ካደረጋቸው ነገሮች (እንደ ሰላት እና መሰል ነገሮች) የማያዘናጋ ከሆነ፣ እና እንዲሁም የተከለከሉ ነገሮችን ያላካተተ ከሆነ — ለምሳሌ፡ አውራትን መግለጥ፣ የሴቶችና የወንዶች መደባለቅ፣ ወይም የሙዚቃ መሣሪያዎች መገኘት — በጨዋታውም ሆነ እሱን በመመልከት ላይ ምንም ችግር (ሀጢአት) የለበትም።
ስኬትም ከአላህ ነው፤ የአላህ ሰላትና ሰላም በነቢያችን ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ይውረድ። »
📗 [ ፈታዋ አል-ለጅናህ አድ-ዳኢማህ (15/238) ]
🌱 @TewhedandSuna