የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
በየኢትዮጵያ የፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 70 መሠረት ክርክሩ እንዲሰማ በተወሰነው ቀነ ቀጠሮ ከሳሽ ቀርቦ ተከሳሹ ያልቀረበ እንደሆነ፡-
1. ለተከሳሹ የተላከለት መጥሪያ የደረሰው መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ በሌለበት የነገሩ መሠማት ይቀጥላል፡፡
2. መጥሪያው በትክክል መድረሱ ያልተረጋገጠ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ሁለተኛ መጥሪያ እንዲላክ ትእዛዝ ይሰጣል፡፡
3. መጥሪያው የደረሰው መሆኑ ቢረጋገጥም እንኳ ለተከሳሹ የተሰጠበት ቀን ለክሱ መልስ ማዘጋጀት በቂ ሆኖ በማይገመት አጭር ጊዜ መሆኑን ፍርድ ቤቱ የተረዳው ሲሆን የክርክሩን መስማት ለሌላ ቀነ ቀጠሮ ያስተላልፈዋል፡፡
4. አንድ ወይም ካንድ በላይ ለሆኑ ተከሳሾች የተላከው መጥሪያ ለተከሳሹ ወይም ከተከሳሹ ወይም ከተከሳሾቹ መካከል ላንዳንዱቹ ሳይደርስ የቀረው በከሳሹ ቸልተኛነት ወይም ጉድለት መሆኑን ፍርድ ቤቱ የተረዳው እንደሆነ መጥሪያው ባልደረሰው ወይም ባለደረሳቸው ተከሳሾች ላይ የቀረበውን የክስ መዝገብ ዘግቶ ለማሰናበትና ነገሩም ይግባኝ እንደሆነ የይግባኙን መዝገብ ለመዝጋት ይችላል፡፡ ተገቢ መስሎ ከታየውም ክሱ የሚሰማበትን ቀነ ቀጠሮ ይለውጣል፡፡ ስለሆነም መጥሪያ ያልደረሰው ተከሳሽ ወይም መልስ ሰጭ ራሱ ወይም ወኪሉ ጉዳዩ በሚሰማበት ቀን ፍርድ ቤት የተገኘ እንደሆነ ወደ ችሎቱ ቀርቦ እንዲከራከር ሊታዘዝ ይችላል፡፡ ይህ ሲሆን መጥሪያ ባለመስጠቱ ምክንያት የሥረ ነገሩ ወይም የይግባኙ ፋይል አይዘጋም፡፡
መጋቢት 7/2014 ዓ.ም (ኦምኒኤል)
Comments
Be the first to add a comment