👉የግንባታ ኢንደስትሪ በኢትዮጵያ

💫የግንባታው ኢንዱስትሪ የተለያዩ ሀብቶችን ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት አስፈላጊ ወደሆኑ የግንባታ ውጤቶች የሚለውጥ እና እሴት የሚፈጥር የኢኮኖሚ ዘርፍ ሲሆን ኢንዱስትሪው የአንድ አገር የማኅበራዊና የኢኮኖሚ መሠረተ ልማት አገልግሎቶች ማለትም እንደ ፋብሪካዎችና የመኖሪያ ቤቶች የመሳሰሉት የሚጠኑበት፣ የሚቀረፁበት፣ የሚታቀዱበት፣ የሚገነቡበትና አገልግሎት ላይ የሚውሉበት ሂደት ነው፡፡ በትግበራውም መንግስታዊ፣ የግል ድርጅቶችና ግለሰቦችን፤ በባለቤትነት፣ በተቆጣጣሪነት፣ በአማካሪነት፣ በሥራ ተቋራጭነት፣ በግንባታ ዕቃዎች አምራችነት፣ በምህንድስና ዕቃዎች አዘጋጅነት፣ መሣሪያዎችና ፋይናንስ አቅራቢነት እና በግብይት ሥራ ላይ የተሰማሩ ባለሚናዎች በሙሉ የሚሳተፉበት ነው፡፡

🚧የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚና የማህበራዊ መሠረተ-ልማት አውታሮችን በማስፋፋት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር እና ሌሎች ዘርፎች እንዲስፋፉና እንዲለሙ በማድረግ የአገሪቱን ኢኮኖሚ የሚያሳድግ ከመሆኑም በላይ ብዙ የፈጠራ ስራዎችና ሳይንሳዊ ግኝቶችም የሚከናወኑበት የኢንዱስትሪ ዘርፍ ነው፡፡

⏺የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ሁለገብ አቅም ማጠናከር የኢኮኖሚና የማህበራዊ መሠረተ ልማት አውታሮችን እና የሥራ ዕድልን በማስፋፋት ረገድ ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ በተጨማሪ የውጭ ምንዛሪን የማመንጨት ሚናም አለው፡፡

⏺የአገር ውስጥ ሥራ ተቋራጮችና አማካሪዎች በአግባቡ ከተደራጁ እና ተገቢውን የመወዳደር አቅም ከገነቡ ለውጭ የሥራ ተቋራጮችና አማካሪዎች የሚከፈለውን የውጭ ምንዛሪ ማዳን እና ደረጃ በደረጃ በፈጠነ መንገድ ከአገር ውጭ ተወዳድረው ሥራ በመሥራት የውጭ ምንዛሪ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

@etconp

Comments

Be the first to add a comment