👉በኮንስትራክሽን ውል የስራ ለውጥ!

በኮንስትራክሽን ውል የስራ ለውጥ(variation) የሚባለው በዋናነት የግንባታ ስራ ጥራትን፣መጠን፣ዲዛይን፣የግንባታ ቁሳቁስ፣የስራ ጊዜ፣የግንባታ ማከናወኛ ቦታ መጠን የመሳሰሉትን የማሻሻል፣የመጨመር ወይም የመቀነስን የሚመለከት የኮንስትራክሽን ውል መሰረታዊ ነጥብ ነው፡፡
*ስለዚህ ቫሬሽን የዋናውን የኮንስትራክሽን ውል ይዘት/object of the contract/ በመጠኑ የመለወጥ ባህሪ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡
*PPA 2011 ክሎስ 15.1 ይሄንኑ አረዳድ በሚያጠናክር ሁኔታ ለቫሬሽን ትርጉም ይሰጠዋል፡፡

ቫሬሽን ኦርደር/variation order/ የሚባለውስ ምንድን ነው? ማነው ኦርደር ሰጭው? በቃል ኦርደር መስጠት ይቻላል? በምን አይነት መልኩ ነው ትእዛዝ የሚሰጥ? በዚህ ረገድ ህጉ ምን ይላል?

*ቫሬሽን ኦርደር ከመሀንዲሱ ለተቋራጩ በጽሁፍ የሚሰጥ የስራ ለውጥ ትእዛዝ ነው፡፡
*አማካሪ መሀንዲሱ ለግንባታ ስራው መልካም አፈጻጸም ሲባል የስራ ለውጥ ትእዛዝ አስፈላጊ ነው ብሎ ካመነ ትእዛዝ መስጠት ይችላል፡፡
*በመጀመሪያ ግን በአማካሪ መሀንዲሱ አማካይነት ለተቋራጩ ስለለውጥ ስራው ባህሪና ምንነት ማሳወቂያ/ኖቲስ/ እንዲደርሰው ይደረጋል፡፡ኖቲስ እንደደረሰው ተቋራጩ የለውጥ ስራውን አስመልክቶ ትሮፖዛል ያቀርባል፡፡ፕሮፖዛሉም የጊዜ ማራዘሚያ/ስኬጁል፣የዋጋ ሁኔታን የሚያካትት ይሆናል፡፡(PPA 15.3)
*የስራ ለውጥ ትእዛዝ በጽሁፍ ነው መደረግ እንዳለበት PPA 2011 ክሎስ 15.2 ያስቀምጣል፡፡አንዳንዴ ግን አማካሪ መሀንዲሱ በቃል የቫሬሽን ትእዛዝ መስጠት እንደሚችል PPA 2011 ክሎስ 15.2(a) ላይ ፈቃጅ ሆኖ ተቀምጧል፡፡ ነገር ግን በቶሎ የለውጥ ስራ ትእዛዙ ወደ ጽሁፍ መቀየር ይኖርበታል፡፡
እዚህ ጋር አብሮ የሚታየው ነገር የአስተዳደር መስሪያ ቤት ጋር የሚደረጉ ውሎች በጽሁፍ መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡ይሄውም ስለውሎች በጠቅላላው በሚመለከተው የውል ህግ አንቀጽ 1724 ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡
*አንድ ውል የሚሻሻለው ደግሞ ከመጀመሪያው ውል ጋር ተመሳሳይ በሆነ ፎርም ነው፡፡በዚህ ረገድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1722 ላይ "ዋናውን ውል የመለወጥ ጉዳይ ለዚሁ ውል በተደነገገው አጻጻፍ(ፎርም) መሰራት አለበት፡፡" በሚል የተደነገገው የሚያስገነዝበውም ቫሬሽን ዋናውን ውል በከፊል የመለወጥ ሁኔታ ስለሚኖረው ከዋናው የኮንስትራክሽን ውል ጋር በተመሳሳይ የአጻጻፍ ፎርም በጽሁፍ መደረግ ይኖርበታል ማለት ነው፡፡ለዚህ ነው በመርህ ደረጃ ቫሬሽን በጽሁፍ መደረግ አለበት የሚባለው፡፡

የስራ ለውጥ ውል/change agreement/ ምን ማለት ነው? ከህግ አንጻር በዚህ ረገድ ምን ነጥቦች ሊነሱ ይችላሉ?

*PPA 2011 ክሎስ 15.9 ላይ እንደተቀመጠው በየስራ ለውጥ ውል የሚባለው ከቫሬሽን ኦርደር በኋላ አሰሪው/ተወካይ መሀንዲሱ እና ተቋራጩ በጽሁፍ የሚስማሙበት የማሻሻያ ውል ነው፡፡ ሆኖም በዚህ የፒፒኤ ትርጉም ጸሀፊው አይስማማም::
ምክንያቱም አማካሪው ስራ ለመቆጣጠር እንጅ ውል ለመዋዋል በአማካሪነት ውሉ ላይ ብዙ ጊዜ ስልጣን አይኖረውም፡፡በተቋራጭና አሰሪ መካከል የተደረገ የኮንስትራክሽን ውል በአሰሪና ተቋራጭ በሚደረግ ስምምነት/ውል ሊሻሻል ከሚችል በስተቀር አማካሪ መሀንዲሱን ውል እንዲዋዋል እስከመፍቀድ የሚደርስ ትርጓሜ መሰጠቱ ተገቢነት የለውም፡፡
*የስራ ለውጥ ውሎች ቀን፣ቁጥርና ቅደምተከተል ይሰጣቸዋል፡፡(ፒፒኤ15.10)
━━━━━━━━━━━━━
‎👉የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሕግ እና አተገባበሩ | የተግባር መመሪያ መፅሐፍ ይፈልጋሉ?
‎
‎📚 ይህ መፅሐፍ በኮንስትራክሽን ሼል ውስጥ የሚመለከቱ የሕግ ጉዳዮችን በቀላልና ተግባራዊ መልኩ ለመረዳት ይረዳል።
‎
⏺‎የኮንስትራክሽን ሕግ መሠረታዊ ግንዛቤ
⏺‎የግንባታ ፕሮጀክት ሕጋዊ አተገባበር
⏺‎የተዋዋይ ወገኖች መብትና ግዴታ
⏺‎የኮንትራት እና የስምምነት ጉዳዮች
⏺‎የግንባታ ሼል ኃላፊነትና ተጠያቂነት
⏺‎በግንባታ ሼል ላይ የሚፈጠሩ የሕግ ጉዳዮች እና ሌሎች ተካተዋል👇
‎
‎https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a83e1c10064f_etconp

Comments

Be the first to add a comment