Ethiopian Construction Vacancy & Tender
👉
ብሔራዊ ግልጽ የግንባታ ጨረታ
ማስታወቂያ 002/2019
🌟
የደቡብ ም/ኢት/ሕ/ክልላዊ መንግሥት በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ሥር ባለው በቡታ ሆራ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት የዲች ቦይ ግንባታ ሥራ ብቁ የሆኑ የGር ወይም የBC ብቃት ማረጋገጫ ያላቸውን ድርጅቶች አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
🚥
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተቀመጡ መስፈርቶችን በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ
- በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያለው :
- ሕጋዊ የሆነ የደረጃ 8 እና ከዚያ በላይ የሆነ የGC ወይም BC የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- ቲን ነምበር ያለውና ቫት ተመዝጋቢ ስለመሆኑ አስረጂ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
-የአቅራቢነት መረጃ ማቅረብ የሚችል፡
-ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ሰነድ አንድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦሪጅናል ሰነድ በታሸገ ፖስታ አድርገው ለእያንዳንዱ ቢያንስ ሁለት ሁለት ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ብር 50,000 /ሃምሣ ሺህ ብር/ ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO/ በአጫራቹ መ/ቤት ሥም አሠርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21/ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብቻ እየከፈለ ከሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ 5 ዘወትር በስራ ሰዓት ሰነዱን ገዝተው መውሰድ ይችላሉ።
- ጨረታው በወረዳችን ላይ በየትኛውም ፕሮጀክት ሥራዎች የጨረታ አሸናፊ በመሆን ውል ገብቶ ሥራውን በመጀመር መቶ በመቶ ያላጠናቀቀውን ማንኛውንም ግንባታ ድርጅት አይመለከትም፡፡
-ጨረታ በ22ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ሕጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት የሚታሸግ ሲሆን በዕለቱ ከጠዋቱ በ4፡30 ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ሕጋዊ ተወካዮቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሰነድ የመክፈት ሂደትን አያስተጓጉልም፡፡
- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ:- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ
ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር
047668-02-00
ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ
የደቡብ ም/ኢት/ሕ/ክልላዊ መንግሥት
በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
@etconp
Comments
Be the first to add a comment