የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ነስና መብዛት በቅጣት አወሳሰን ላይ ከመጠቀም ባለፈ ከድርጊቱ አስቀጪነት ነጻ አያወጣም፡፡ እንደዚሁም እንደ ልማድ(hobby) ገንዘብ የምትሰበስብ ሰው መሆንህን ህጉ ለይቅርታ ምክንያት አድርጎ አላስቀመጠውም፡፡
በዚህም ህግ አውጪውና የብሔራዊ ባንክ ገዢዎች የህግ መሰረታዊ ባህሪ የሆነውን የህብረተሰብን መልካምና ጤነኛ ባህልና ልማድን ዕውቅና መስጠት ማስከበርና መጠበቅ ያላገነዛበ ድንጋጌዎችን በማውጣት የግለሰብን መብት ባለማክበር ማህበረሰብ ለሞራል ህግ ተገዢ እንዳይሆን ዱላ እያቃበሉ ነው፡፡
ለ/ የፍትህ ሚኒስትር ሰሩኩላር
ነገር ግን የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር(ጠቅላይ ዐቃቤ-ህግ) ይህ ከላይ የተመለከተው አዋጅና መመሪያ መሰረታዊ የግለሰቦች መብት ላይ ጥሰት የሚያስከትል መሆኑን ዕውቅና በመስጠት በ2011ዓ.ም ባወጣው ሰርኩላር (ይህን ለማግኘት ያደረኩት ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም) በኢትዮጵያ ሲመነዘሩ የገንዘብ መጠናቸው ከብር 1,000(አንድ ሺ) በታች የሆኑ በኢትዮጵያ ለክፍያ መዋል የሚችሉ ማንኛውም የውጪ ሀገር ገንዘቦችን በያዙና ባስቀመጡ ሰዎች ላይ ክስ እንዳይቀርብና ፣የቀረበ ክስ ካለም እንዲቋረጥ አድርጓል፡፡ ይህን ጽሁፍ በማገባደድ ላይ እንዳለሁ የፍትህ ሚኒስቴር ይህን ሰርኩላር በማሻሻል መጋቢት 15 ቀን 2014ዓ.ም በቁጥር ፍ/ሚ 01ደማ3066 በተጻፈ ሰርኩላር ይህን የገንብ መጠን ልክ ወደ 100(አንድ መቶ ) የአሜሪካን ዶላር ከፍ ወይም አሁን ባለው የባክ ምንዛሬ ሲመነዘር ከ5,200(አምስት ሺ ሁለት መቶ) በታች ከሆነ ገንዘቡ እንዲወረስ ክስ ግን እንዳይቀርብ አሳውቋል፡፡ ልብ አድርግ ክስ እንዳይቀርብ እንጂ ድርጊቱ ወንጀል አይደለም አልተባለም፡፡ በዚህም ተግባሩ የግለሰቦች ጤናኛ ልማድን አክብሮ ጤናኛ ማህበረሰብ እንዲገነባ ፍትህ ሚኒስቴር መሰረት ጥሏል፡፡
3. ትግበራ
ህጉ በተለይም ደግሞ የፍትህ ሚኒስቴር ሰርኩላር ደብዳቤ ተፈጻሚ እየሆነ ባለበት ሁናቴ የራሱ የተቋሙ ሰራተኞች ከላይ ለዚህ ጽሁፍ ምክንያት የሆነውን ክስ ማቅረባቸው ተቋሙና ሰራተኞቹ የትና የት ናቸው? የሚያሰብል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ እኔም የተቋሙን ሰርኩላር መሰረት በማድረግ ጉዳዩን ለበላይ አካል በማሳወቅ ከ8ወራት የፍርድ ቤት ምልልስ በኃላ ክሱ ተቋርጦ መዝገቡ ተዘግቶ ተሸኘን፡፡ ይህ አንድ ጉዳይ የትግበራው ሙሉ ሂደትን ለማስቃኘት በቂ እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡ ቢሆንም ሀሳቤ እንደ ሁልጊዜው የገጠማችሁን እንድታካፍሉንና ልማድን በዕውቀት እንድንሽር ነውና ዝምታቹን ስበሩ፡፡
Comments
Be the first to add a comment