🌱 ፆታ ሲሆን smart ዘር ሲሆን ዘረኛ
• የዘረኝነት
ትልቁ ችግር ሰዎች በራሳቸው ባላመጡት ማንነት ላይ ለመመፃደቅ መሞከራቸው አልፎም ሌሎችን አንቋሾ መመልከታቸው ነው፡፡
ብዙዎቻችን ዘር ሲሆን ይህን የዘቀጠ አስተሳሰብ እናስተውላለን፡፡
ነገር ግን አላህ ወደ ሰጠን ፆታ ስንመጣ በራሳችን ያገኘነው ይመስል፤ "ወንድኮ" "ሴትኮ" እያልን እንበሻሸቃለን፡፡
የተሰጠንን ሐላፊነት ከመወጣት ይልቅ በእንቶ ፈንቶ ክርክሮች፣ አላማ ቢስ በሆኑ ፉከራዎች እና መበሻሸቆች ጊዜያችንን እናጠፋለን፡፡
አንድ ሰው እኔ ከሌሎች የተሻለ “የሆነ ነገር” አለኝ ካለ፤ በዛ ነገሩ ሌሎችን ምን ጠቀመ፣ ለራሱስ ምን ተጠቀመ የሚለው እንጂ “አለኝ” እና “ነኝ” ማለቱ ብቻ ጥቅም የለውም፡፡
የተሻለ ነገር ኖሮት ምንም ካልሰራበት ደግሞ ሳይኖረው ከተቀመጠ ሰው የበለጠ ውርደት ላይ ነው፡፡ አላህ በሰጠን ማንነት ከመመፃደቅ ወጥተን ከኛ ምን ይጠበቃል ላይ እንበርታ!!!
© huneynn
•
@TewhedandSuna