👉በ ግንባታ ላይ ስላለው ወቅታዊ የሰራተኞች እጥረት በተመለከተ ጥቂት ለማለት ...

ለዚህ ጽሁፍ ዋናው መነሻዬ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴራችን ስለ በግንባታ ላይ ስለሚታየው የሰው ሃይል እጥረት የተናገሩትን በማድመጤ ነው።

በዘርፉ ውስጥ ስለሆነ ያለሁት በየዕለቱ የሚገጥመንን የባለሙያና የቀን (የጉልበት) ሰራተኛ እጥረትን በትክክል በማስቀመጣቸው ከተናገሩት ጋር 100% ስምምነኝ። በጥሩ ተረድተውታል ብዬ አምናለሁ።

ብዙ ወጣቶች ወደ ግንባታው ዘርፍ ከጉልበት ሰራተኛነት ጀምሮ በተለያየ ሙያ በተግባር እየሰለጠኑ ቢቀላቀሉ ለጋሳቸው የተሻለ ገቢ እያገኙ ለሀገራቸውም ጥሩ ገንቢ በመሆን የኑሮ እንቆቅልሻቸውን መፍታት እንደሚችሉ ቋሚ ምስክር ነኝ።

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ ላለፉት 27ዓመታት ሳሳልፍ የማውቃቸው አብረውኝ ከሃያ ዓመታት በላይ የሰሩ የግንባታ ባለሙያዎች የኑሮ ደረጃን መሻሻል እንደቤተሰብ ተቀራርበን አሁንም እየሰራን እለምንኖር የኑሮ ለውጣቸው ምስክር ነኝ።

ከጥቂቶቹ በስተቀር ቤት ሰርተው ወይም ገዝተው የሚኖሩ ናቸው።

እንደውም በቅርቡ አንዱ ፌራዮ 40/60 ኮንዶሚኒየም ካሽ 6.7ሚሊየን ከፍሎ ሲገዛ አማካሪው እኔ ነበርኩ፣ተጨማሪ ሰው አስልጥነው ቀጥረው የሚያሰሩ፣ ቤተሰባቸውን ኑሮ ውድነት ሳይፈታተናቸው የሚመሩ፣ ቤታቸው ሙሉ የሆነ፣ ልጆቻቸውን በግል ዩኒቨርስቲ ጭምር ከፍለው የሚያስተምሩ፣ አሱዙ ገዝተው ሹፌር ቀጥረው በደቡብ ክልል ለስራ ያሰማሩ ፣ በከተማችን ለራይድ የሚሆን መኪና ገዝተው በትርፍ ጊዜያቸው የሚሰሩ....በርካቶችን አውቃለሁ።

ይህ ጥቂቶች ቆራጦች ጉልበታቸውን ሳይቆጥቡ ፣ ሌት ተ ቀን ፍግት ብለው የሚሰሩበት፣ ቱታ ለብሰው ውለው ቁርጥ በልተው ለጥማቸው ድራፍት ተጎንጭተው የመዋል አቅም ያላቸው ..... ወገኖች ቁጥር ለምን አነሰ? ብለን ብንጠይቅ የሚከተሉትን መላ ምቶች ከውሏችንና ከኑሯችን መምዘዝ እንችላለን

1) ቀለል ያለ ስራ ለመስራት መምረጥ
2) የግንባታ የሙያ ስራን ( አናጢ፣ ግንበኛ...) ከ ክፍለ ሃገር ለሚመጡ ወገኖች ብቻ ነው ብሎ ማሰብ
3) የሚገኝበት ጥቅም አለማወቅ ። በዚህ ወቅት የቀን ሰራተኞች ( የጉልበት ስራ) 800 እስከ 1200ብር ፣ ለአናጢ አማካይ ክፍያ 1500ብር...
4) ለሙያው የሚሰጠው ክብር ማነስ። ይህ ቀድሞ ከነበረ የስራና የተማሩ ሰዎች ማክበሪያ መስፈርት መበላሸት።
5) ዘርፉ በስልጠና አለመታገዙ። እኔ ደርሶብኝ የማውቀው ለማሰልጠን ቢፈለግም በፈቃድ ሰጪ አካላት የሚጠየቀው መስፈርት መብዛት።
6) በሙያቸው ደረጃ እየተመዘኑ የሚሰጥ አበረታች የሙያ ማስመስከሪያና ማረጋገጫ ሰጪ አካል አለመኖር....
7) በሙያው የሚሰማሩ ባለሙያዎች ረዘም ላለ ጊዜ በሙያው ከመዝለቅ ይልቅ የተወሰነ ገንዘብ ይዘው ወደ ንግድ፣ ሹፍርና፣ግብርና የመሳሰሉት ዘርፎች ለመግባት መፈለጋቸው

እና ምን  ይጠበስ?

በእኔ ዕይታ የሚከተሉት ቢታሰብባቸው ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ

1) መንግስት ችግሩን ከተረዳው ዘንድ በሙያና ስልጠና ላይ በትኩረት ቢሰራ ።
2)ስልጠና ለመስጠት ለፈቃድ የወጡ መስፈርቶችን የህንድን ሳይሆን የሀገራችንን ሁኔታ ያገናዘበ እንዲሆን ቢደረግ
3) ስልጠናውን የሚሰጡ ተቋማትን የሚከታተሉና ፈቃድ የሚሰጡ የስራው ሂደት መሪዎች ዘርፉን የሚያውቁ በግንባታ ውስጥ ያለፉ ባለሙያዎች ቢመራ
4) የባለሙያዎች ዋና ተጠቃሚ የሆኑ ታላላቅ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች የባለሙያዎች ማሰልጠኛ ከፍተው በፕሮጀክቶቻቸው ውስጥ ብቁ የሚያደርግ ስልጠና መስጠት ቢጀምሩ።
5) የስራ ተቋራጮች ማህበር ከመንግስትና የዘርፉ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የሙያ ስልጠናና ምዘና እንዲካሄድ ግምባር ቀደም ሆኖ ቢመራ ቢከተል።
6) በሳይት ላይ ተግባራዊ ልምምድ በማግኘት ራሳቸውን ብቁ ያደረጉ ባለሙያዎች የተለያዩ ምዘናዎች በመስጠት የብቃታቸው ማረጋገጫ ደረጃ እየተሰጣቸው ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነታቸውን ማሳደግ
7) ከተለምዷዊው የሙያ ስልጠና በተጨማሪ ዘመኑን ያማከለ የግንባታ ላይ ደህንነትን ያካተተ የተለያዩ የስካፎልዲንግ ገጠማና አጠቃቀም፣ ዘመናዊ የመለሰኛ ማሽኖች አጠቃቀም፣ የገንዘብ አያያዝና አጠቃቀም....አካትቶ በየጊዜው ብቃት ማሳደጊያ ስልጠና ቢሰጣቸው።

በ ደሳለኝ ከበደ መሀንዲስ፣ ገንቢ፣ አሰልጣኝ እና ሪል ስቴት አማካሪ

@etconp

2 comments

Zemen. T
ሀሳቡ ጥሩ ነው።
በእየለቱ ምትለቃቸው መረጃዎች እና እውቀት አዘል ምክሮች ጥሩ ናቸው።በግሌ አመሰግናለሁ።
ነገር ግን ምናልባት አንተ ስራው ላይ የቆየኸው እረጅም ግዜ ስለሆነ በስራው እንደወቅቱ ሁኔታ በሚገባ የተጠቀምህበት ይመስለኛል።
የእኔ አስተያየት ግን አሁን ላይ ካለው በተለይም ከቅርብ አመታት ጀምሮ ያለውን የዘርፉ ሁኔታ እና የሰራተኛ ጥቅም ጋር ያለው ሁኔታ ላይ ነው።
በዚህም መሰረት
1.አሁን ላይ ባለሙያው እንደባለሙያ እየተከበረ አይደለም የሚገባውንም ጥቅም እያገኘ አይደለም።ይህ ማለት የቀን (የጉልበት) ሰራተኛው ስራውን የሚከውነው ቁልፍ ነገር ቢሆነም ዋና ባለሙያው ደግሞ ትክክለኛ ቦታ እና አስፈላጊው ነገር ሊሟላለት ይገባል ባይ ነኝ።

2. ዘርፉ ከትክክለኛው ባለሙያ ውጭ የሚመራ ሆኗል።ባለሙያው ሌላው ብር ያለው (ባለቤቱ) አልያም በዘልማድ የመጣ የባለሀብቱ ቤተሰብ ይሆናል።ባለሙያው ወይም ባለውቀቱ ለእንጀራ ሲል ብቻ የተባውን ሰሪ አልያም ጉዳይ አስፈፃሚ ብቻ ሆኖ እንዲያገለግል ይደረጋል።በዚህም የተነሳ ከስራ ማጣቱ በተጨማሪ ባለሙያው በሙሉ ከዘርፉ እየወጣ በሌ መንገድ እየተሰማራ ነው።
ምን ለማለት ነው Client ላይ ትንሽ ጠበቅ ያለ ህግ ወጦ ሙያው የሚከበር ቢሆን።

3. የሀገሪቷ የኮንስትራክሽን ህጎች በየፕሮጀክቱ ተከብረው ሳይሸራረፉ እንዲተገበሩ እና የዘርፉ የስራ ፍቅር እንዲጨምር ከተፈለገ።።።ባለሙያው ሙሉ ክብር :ሀላፊነት እና ጥቅሙ የተከበሩ መሆን አለበት።

4. የአንድ ፕሮጀክት ስራ ከፈቃድ እስከ ግንባታው መጠናቀቅ ድረስ ያለው ሂደት ትክክለኛ እና እውነተኛ ህግንና መመሪያን ያከበረ ወጥነት ያለው መሆኑ መረጋገጥ አለበት።እንጂ ባለቤቱ ወይም የባለቤቱ ተወካይ ከፈቃድ በኋላ እንደፈለገው የሚቀያይረው እና በገንዘብ ድለላ የሚያስጨርሰው መሆን የለበትም።

5. በአጠቃላይ ዘርፉ ክብሩን ጠብቆ ከባለሙያ እስከ የቀን(የጉልበት) ሰራተኛ የሚወደድ እና የሚከበር መሆን አለበት።

እንደ አንድ የዘርፉ ባለሙያ የግል አስተያየቴ ነው።
አመሰግናለሁ።
biruk Bekele
እኔ ግን አንተ በሚትለው አልስማማ።
የታነገርኮው ሁሉም የምሆን ብሆን ለእኔ ብሆን ነበር።ከልጅናት እስከ ሹምግልና ሰረቼሎ ግን ልውጥ ሰይሆን በህይወት ጠብ የለው ነገር አለየሁም።እንቴ ግን ጨርታ እንኮን የለጉቦ አሸንፋ አተውቅም ።ለምን ትወሸለ ።ስራ ሰረታህ ጉቦ ሰትከፍል ታረክቦ የወቃል ስፒርበዘር።ለምን እንወሸሌን።እትዮጵያ ውስጥ የሉ ትልቅ construction ውስጥ ሰረቼ አይቼለው ።አንድ ስታት ሰይሰር የለፈ አይቼ አለውቅም ቀን ሰረታኛ ሰይሆን እንኮን መንድሰችም።አንተ ትርንስፎርት እንኳን መሸፈን የመችለውን ስለማትከፍል ነው።1200-1500ድርስ ይከፈላል ።ምን ይገዘል ።አንተ አንድ ነገር አዘህ ስንት ከፍለ ነው የምትውጠው።