👉የሕንፃ ግንባታ ደህንነትን ሳይጠብቁ በሚሠሩ አልሚዎች ላይ ጥብቅ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተገለጸ!

🌟​በአዲስ አበባ ከተማ የሕንፃ ደህንነት መስፈርቶችን ሳያሟሉ እና ለአደጋ አጋላጭ በሆነ መልኩ ግንባታዎችን ሲያካሂዱ በተገኙ አልሚዎች፣ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ላይ የገንዘብ ቅጣትና አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃ መወሰዱን የከተማ አስተዳደሩ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ።

​የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የክትትልና ቁጥጥር ዘርፍ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር አመለወርቅ አሰፋ እንደገለጹት፤ በከተማዋ በተከናወኑ የመስክ የቁጥጥርና ክትትል ሥራዎች ሕግን እና የደህንነት ደንቦችን አፍንጫቸው ስር ጥሰው የሚገኙ አካላት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል።

🚥​በዚህም መሠረት፡-

​በአልሚዎች ላይ፦ ሕጋዊ የደህንነት መስፈርቶችን ባላሟሉ አካላት ላይ የገንዘብ ቅጣት ተጥሏል።

​በኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ላይ፦ ተገቢው ጥንቃቄና ቁጥጥር ሳያደርጉ ቀርተዋል ተብሎ የታመነባቸው ላይ አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃዎች ተወስደዋል።

​የደህንነት ጥንቃቄ ለሕይወትና ለንብረት ዋስትና ነው!

​እንደ ኢ/ር አመለወርቅ ማብራሪያ፣ የሕንፃ ደህንነት መስፈርቶችን ሳይከተሉ የሚከናወኑ ግንባታዎች በሥራ ላይ ባሉ ሠራተኞች፣ በአካባቢው ማህበረሰብ እና ነዋሪዎች ላይ ሕይወት የማጥፋት፣ የአካል ጉዳት የማድረስ እንዲሁም በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት የማስከተል አደጋቸው ከፍተኛ ነው።

​"የሕንፃ ግንባታ ደህንነትን ማስጠበቅ የሁሉም ኃላፊነት ነው፤ ሕግን ማክበር ሕይወትን ይጠብቃል" ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፣ መሰል የቁጥጥርና የክትትል ሥራዎች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አሳስበዋል። በመሆኑም ሁሉም አልሚዎች፣ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ሕንፃዎችን ሲገነቡ የደህንነት ጥንቃቄዎችን ሙሉ በሙሉ አሟልተው እንዲሠሩ ጥሪ ቀርቧል።
​
─────────────────
👉Construction Safety & Compliance Kit – ፕሮፌሽናል Safety Templates ጥቅል ይፈልጋሉ?🦺

📋 Safety Checklists
🗣️ Toolbox Talk Templates
📝 Incident Report Forms
⚠️ JSA Templates
🥾 PPE Inspection Sheets

✅ Editable Word Document👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a88471586c15_etconp

Comments

Be the first to add a comment