👉Caterpillar የተሰኘው የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች አምራች ድርጅት በተሽከርካሪዎቹ ላይ AI Automation መግጠም መጀመሩን አስታውቋል።

"Cat AI Assistant" የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ሲስተም የተሰራው Jetson Thor በተሰኘ የNvidia physical AI አማካኝነት ነው።

ከግዙፉ የAI Hardware አምራች ድርጅት NVidia ጋር በመተባበር መካከለኛ መጠን ባላት CAT 306 CR Mini ኤክስካቫተር በመግጠም ለእይታ አብቅቷል።

በ Caterpillar የ Dataና AI ምክትል ፕሬዘዳንት የሆነው Brandon Hootman እንደተናገረው CAT AI assistance የማሽን ኦፕሬተሩን ጥያቄዎች መመለስ፣ የደህንነት መረጃዎችን መስጠት፣ስራዎችን ማቀድ እንዲሁም የተለያዩ የሳይት መረጃዎችን በመሰብሰብ አንድ project ምን ያክል የግንባታ እቃዎች እንደሚያስፈልጉት calculate ማድረግ ይችላል።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment