✿ የአስሩ የዙል ሂጃህ ቀናት ታላቅነት
• ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- “
ከዱንያ ቀናት ሁሉ በላጩ (የዙል ሂጃህ) አስር ቀናት ናቸው።”
▢ በዱንያ ካሉ ቀናት ሁሉ በእነዚህ ቀናት የሚሰሩ መልካም ስራዎች በአላህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ እና ታላቅ ምንዳ የሚያስገኙ ናቸው።
• ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- “
በእነዚህ ቀናት (በመጀመሪያዎቹ አስር የዙል ሂጃህ ቀናት) እንደሚሰራ መልካም ስራ በአላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆነ ስራ ያለበት ሌላ ቀን የለም።”
ሰሃቦችም እንዲህ ሲሉ ጠየቁ፡- “
የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጅሃድም ቢሆን (ከእነዚህ ቀናት መልካም ስራ አይበልጥም)?”
እሳቸውም እንዲህ አሉ፡- “
በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጅሃድም ቢሆን (ከእነዚህ ቀናት ስራ አይበልጥም)፤ በነፍሱና በገንዘቡ ወጥቶ ከሁለቱም ምንም ሳይዝ የተመለሰ (የተሰዋ) ሰው ቢሆን እንጂ።”
▢ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ አስር የዙል ሂጃህ ቀናት የመታዘዣ ወቅቶች እና ለአምላኪዎች ታላቅ እጥፍ ድርብ ምንዳ የሚገኝባቸው ናቸው። እነዚህ ቀናት የሰውን ልብ ክፍት ያደርጋሉ፤ ይህም በቀሪው የዓመቱ ክፍል በታዛዥነት ላይ እንዲጸና ይረዱታል።
🌱 @TewhedandSuna