👉ድርድር (Negotiation)🏗

- በግንባታ ሥራዎች እና ዕቃ ግዥ (Procurement of Works ተand Goods) ግልጽ ጨረታ ላይ፣ ከተጫራቾች ጋር በዋጋ፣ በቴክኒክ ዝርዝር ወይም በውል ሁኔታዎች ላይ መደራደር የተከለከለ ነው፤ ግዥ ፈጻሚው አካል መስፈርቱን አሟልቶ ዝቅተኛ ዋጋ ካቀረበው ተጫራች (Lowest Evaluated Bidder) ጋር ያለምንም ድርድር ውል ማሰር ይኖርበታል።

- አንዳንድ ተቋማት ከፍተኛ ገንዘብ የሚወጣባቸው ግዥዎች ላይ pre-contract award discussion የማድረግ ልምድ አላቸው። ነገር ግን ይህ ድርድር አለመሆኑን ማረጋገጥ ይገባል

- በአንጻሩ፣ የምክር አገልግሎት ግዥ (Procurement of Consultancy Services) የአእምሮ ውጤትና ረቂቅ ባሕሪ ያለው በመሆኑ፣ በቴክኒክና ፋይናንስ ግምገማ አንደኛ የወጣው አማካሪ ድርጅት ተለይቶ ውል ከመፈረሙ በፊት የጋራ ስምምነት ላይ ለመድረስ ሕጋዊ የድርድር መድረክ ይዘጋጃል።

- በምክር አገልግሎት ድርድር ወቅት ትኩረት የሚሰጠው የምክር አገልግሎት ድርድር (Consultancy Negotiation) ሊያተኩርባቸው የሚገቡ ሥራው ዝርዝር ይዘት (Scope)፣ በአፈጻጸም ዘዴ (Methodology)፣ በባለሙያዎች የሥራ ምደባ ሰሌዳ (Staff Months/Schedules)፣ ጥቅም ላይ በሚውሉ ግብዓቶች እንዲሁም በሚቀርቡ ሪፖርቶች ይዘትና አቀራረብ ላይ ብቻ ያተኩራል።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment