#ለኢንጅነሮች‼️

======///=========
🏣👷‍♂️🏛🏢🏤🏣🏛👷‍♀️🏢🏤
#አንድ Client ሬሾው 1:2:3 በሆነ 60m3 የሚሆን የኮንክሪት ስራ ቢኖረውና ስንት ስሚንቶ አሸዋና ጠጠር እንደሚያስፈልገው  በዝርዝር ማወቅ ፈለጎ ስራልኝ ቢላችሁ እንዴት ትሰሩለታላችሁ?  Dry volume factor 1.54

#መልስ
➛ የተሰጠን ዳታ
ጠቅላላ የኮንክሪት ስራ መጠን 60ሜ3
Mix ratio 1:2:3
Assume dry-volume proportion 1.54
➛ከዚህ በመቀጠል ለ1ሜ3  ኮንክሪት የሚያስፈልገን የኮንክሪት ማተርያል እናስላ።

በመጀመርያ የሚከተሉትን እንያዝ
➛1ሜ3*1.54 = 1.54ሜ3
➛Total proportion = 1+2+3 = 6parts

1. #የስሚንቶ መጠን ለማወቅ
   ➛ስሚንቶ፦ 1/6*1.54ሜ3 = 0.257ሜ3
በመቀጠል ይሄንን volume assumption በወሰድነው density of cement 1400kg በማባዛት በKg ወይም በ Number of bags ማማወቅ እንችላለን በዚህ መሰረት፦
🔨 ስሚንቶ≈ 1400ኪ.ግ/ሜ3 * 0.257ሜ3
                         ≈  359.8 ኪ.ግ
     በማጠጋጋት   ≈ 360ኪ.ግ ወይም 3.6ኩንታል ወይም
                            7.2ከረጢት ለ 1 m³ concrete.

2. #የአሸዋ መጠን ለማወቅ
➛በተሰጠን ሬሾ መሰረት አሸዋ 2parts ስለሆነ በቀላሉ ከላይ ያሰላነው የስሚንቶ volume በሁለት በማባዛት ማግኘት እንችላለን።
🔨 አሸዋ ≈ 2* 0.257ሜ3
          ≈ 0.514ሜ3 ለ 1 m³ concrete.

3. #የጠጠር መጠን ለማወቅ
➛በተሰጠን ሬሾ መሰረት ጠጠር 3parts ስለሆነ በቀላሉ ከላይ ያሰላነው የስሚንቶ volume በሶስት በማባዛት ማግኘት እንችላለን።
🔨  ጠጠር ≈ 3* 0.257ሜ3
          ≈ 0.771ሜ3  ለ 1 m³ concrete.

4. #የውሃ መጠን
➛ እዚጋ ማስቸዋል ያለብን ነገር amount of water cannot be determined from the ratio 1:2:3 alone because it depends on the required workability, aggregate moisture, cement type, and water/cement ratio.
➛የ ውሃና ስሚንቶ ሬሾ (W/C ratio) በmix design የሚወሰን ቢሆንም ባብዛኛው ግዜ ግን ከ 0.4 እስከ 0.6 ባለው ሬንጅ ውስጥ ነው።
➛በዚህ መሰረት በአማካይ 0.5 ብንወስድ ለ1ሜ3 ኮንክሪት የሚያስፈልገንን የውሃ መጠን ለማወቅ በቀላሉ
w/c = 0.5    
w/0.257ሜ3 = 0.5
w = 0.5*0.257ሜ3
w = 0.1285ሜ3 ወይም በ1000 በማባዛት128.5ሊትር ያስፈልገናል ማለት ነው።

🔑 ሲጠቃለል ለ60ሜ3 የኮንክሪት መጠን
➛ስሚንቶ 3.6ኩንታል*60= 216ኩንታል
➛አሸዋ 0.514ሜ3*60= 30.84ሜ3 በማጠጋጋት 2ቢያጆ
➛ጠጠር 0.771ሜ3*60= 46.26ሜ3 በማጠጋጋት 3ቢያጆ
➛ውሃ 0.1285ሜ3*60= 7.71ሜ3

@ETCONpWORK

Comments

Be the first to add a comment